አፍሪካ በሪዮ 2016 ፡ ናይጄሪያ ስታሸንፍ አልጄሪያ ተረታለች

የሪዮ ኦሎምፒክ የእግርኳስ የምድብ ጨዋታዎች ሃሙስ ተጀምረዋል፡፡ የአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች ቻምፒዮኗ ናይጄሪያ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች አልፋ ድል ስትቀዳጅ አልጄሪያ ተሸንፋለች፡፡ ደቡብ አፍሪካ አዘጋጇ ብራዚልን ነጥብ አስጥላለች፡፡

ጨዋታው ሊጀመር ስድስት ሰዓታት ብቻ ሲቀሩት ማናስ ከተማ መድረስ የቻሉት ናይጄሪያዎች ጃፓንን 5-4 ማሸነፍ ችለዋል፡፡ የናይጄሪያን የድል ግቦች ኦግንካሮ ኤቴቦ (4) እና ሳዲቅ ኦማር ሲያስቆጥሩ ጃፓንን ከመሸነፍ ያላዳኑ አራት ግቦችን ሺንዞ ኮሮኪ፣ ታኩሚ ሚናሚኖ፣ ታኩማ አሳኖ እና ሙሻሺ ሲዙኪ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ ከ1996 የአትላንታ ኦሎምፒክ በኃላ ወርቅ ለማግኘት ግምት ያገኙት ናይጄሪያዎች በምድብ ሁለትን ይመራሉ፡፡ በዚህ ምድብ ሌላ ጨዋታ ኮሎምቢያ ከስዊድን 2 አቻ ተለያይተዋል፡፡

PicsArt_1470384617228

የግብ ጠባቂ እና የተከላካዮች ያለመናበብ አልጄሪያን ሽንፈት እንድትቀምስ አስችለዋል፡፡ በምድብ አራት ጨዋታ የማዕከላዊ አሜሪካ ሃገሯ ሆንዱራ ሰሜን አፍሪካዎቹን 3-2 በሆነ ጠባብ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል፡፡ ሆንዱራስ በመጀመሪያው አጋማሽ በሮሜል ኩዌቶ እና በማርሴሎ ፔሬራ ግቦች ቀዳሚ ስትሆን አልጄሪያ በሁለተኛው አጋማሽ ውጤቱን በሶፊያን ቤንባካ ግብ ማጥበብ ችላ ነበር፡፡ አንቶኒ  ሎዛኖ ልዩነቱን ሲያሰፋ የእግርኳስ ህይወቱን በካታር ያደረገው አጥቂው ባግዳድ ቦንድጃ አልጄሪያን ከመሸነፍ ያለዳነች ግብ በ84ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡

የአልጄሪያው ግብ ጠባቂ ፋሪድ ቻል የሰራቸው ስህተቶች ለሁለተኛው እና ሶስተኛው ግብ መቆጠር ምክንያት ናቸው፡፡ ፋሪድ የዋናው ግብ ጠባቂ የአብደልቃድር ሳሊ በልምምድ ሜዳ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት የተተካ ግብ ጠባቂ ነበር፡፡ ምድቡን አርጀንቲናን 2-0 ማሸነፍ የቻለችው ፖርቹጋል ትመራዋለች፡፡

PicsArt_1470384597373

ደቡብ አፍሪካ አዘጋጇ ብራዚልን ተቋቁማ አንድ ነጥብ ይዛ ወጥታለች፡፡ በመጀመሪያው አጋማሽ ደቡብ አፍሪካ ከተጠበቀው በላይ ጥሩ የተንቀሳቀሰች ሲሆን በሁለተኛው አጋማሽ ብራዚሎች የጨዋታ እና የግብ ሙከራ የበላይነትን ነበራቸው፡፡ የደቡብ አፍሪካው ግብ ጠባቂ ኢቱሜንግ ኩኔ አደገኛ ሙከራዎችን በማክሸፍ ወሳኝ ሚናን ተወጥቷል፡፡ ተከላካዩ ሞቶቢ ማቫላ በ59ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ ከሜዳ ተወግዷል፡፡ በምድቡ ሌላ ጨዋታ   ኢራቅ ከዴንማርክ 0-0 ተለያይተዋል፡፡

1 Comment

Leave a Reply