‹‹የኮከብ ግብ አግቢነት ክብሩ ከሻምፒዮንነታችን በኃላ የሚመጣ ነው›› ኡመድ ኡክሪ

በሊጉ 7 ጨዋታዎችን አድርጎ 7 ግቦች ያስቆጠረው ኡመድ ኡኩሪ አሁን በሊጉ የሚፈራ አውራ አጥቂ ሆኗል፡፡ እሁድ እለት አርባምንጭ ላይ አርባምንጭ ከነማን 1-0 በረቱበት ጨዋታ ብቸኘዋን ግብ ከመረብ ያሳረፈው ኡመድ የውድድር አመቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ አስደሳች እንደሚሆን ለሀት-ትሪክ ጋዜጣ ተናግሯል፡፡

‹‹ የአርባምንጭ ጉዟችን በፈተና የተሞላ እንደሚሆን ገምተን ነበር፡፡ ነገር ግን ተጋጣሚያችንን እንደጠበቅነው ጠንካራ ሆኖ አላገኘነውም፡፡ በርካታ የግብ እድሎችን እንደመፍጠራችን ጨዋታው በሰፊ ግብ መጠናቀቅ ነበረበት፡፡ ያ ባለመሆኑ አርባምንጮች እድለኞች ነበሩ፡፡››

‹‹ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቀድሞውንም የሊጉን ዋንጫ ለማግኘት አይቸገርም፡፡ አምና ዋንጫውን አሳልፈን በመስጠታችን ሁላችንም አዝነናል፡፡ ዘንድሮ እኔን ጨምሮ በርካታ ተጫዋቾች ለቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የመጀመርያ የሊግ ድላችንን ለማሳካት ከፍተኛ ጉጉት አድሮብናል፡፡ ከለቡም እያዳንዷን ጨወታ በትኩረት ስለሚመለከታት ወደዋንቻው እናመራለን›› ሲል አጥቂው በቡድኑ እንደሚተማመን ገልጻል፡፡

አምና በውድድር ዘመኑ ሙሉ ያስቆጠራቸው የሊግ ግቦች ላይ ለመድረስ ከወዲሁ 2 ግብ ብቻ የቀረው ኡመድ የኮከብ ግብ አግቢነቱን ከተከታቴቹ በ3 ግቦች ርቀት ላይ ተቀምጦ ቢመራም ቅድሚ የሚሰጠው በእያንዳንዱ ጨዋታ ለቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናፊነት ያለውን መስጠት ነው፡፡

‹‹ ክለቡ ጨዋታዎችን እንዲያሸንፍ የምችለውን አደርጋለሁ፡፡የዘንድሮ አላማዬም ቅዱስ ጊዮርጊስ የሊጉን ዋንጫ እንዲያገኝ መርዳት ነው፡፡ የሊጉን ግብ አግቢነት እየመራው ቢሆንም ቀዳሚ አላማዬ ቅዱስ ጊዮርጊስን ውጤታማ ማድረግ ነው፡፡ ››

{jcomments on}