ሀዋሳ ከተማ የ17 አመት በታች የሁለትዮሽ አሸናፊ ሆኗል

የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ጥሎ ማለፍ በትላንትናው እለት ፍጻሜውን ሲያገኝ ሀዋሳ ከተማ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል፡፡

በቦዲቲ ስታድየም በወላይታ ድቻ እና ሀዋሳ ከተማ መካከል በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 3-3 ተጠናቋል፡፡
ልጅአለም መላኩ ፣ ሲሳይ ማሜ እና ክብሩ በለጠ ለወላይታ ድቻ ሲያስቆጥሩ ያሬድ መሃመድ (ፍቅም) ፣ ገብረመስቀል ዱባ እና እስራኤል እሸቱ ለሀዋሳ ከተማ አስቆጥረዋል፡፡

PicsArt_1470663671619

አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የመለያ ምት ሀዋሳ ከተማ 4-2 በማሸነፍ የውድድር ዘመኑን በሁለትዮሽ ዋንጫ ደምድሟል፡፡ የሀዋሳው ግብ ጠባቂ አላዛር መርኔ 2 የመለያ ምቶችን በማዳን ለቡድኑ አሸናፊነት ትልቁን ሚና ተወጥቷል፡፡

ሀዋሳ ከተማ በ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ የዞኑን እና የማጠቃለያ ውድድሩን በቻምፒዮንነት ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *