የኢትዮዽያ ብሄራዊ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር በባቱ ከተማ ሲቀጥል ወደ ከፍተኛ ሊግ የሚገቡ የመጨረሻ 2 ክለቦች የተለዩባቸው ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡
08:00 ላይ በተካሄደው የመጀመርያ ጨዋታ ካፋ ቡና እና መተሀራ ስኳር በመደበኛው ክፍለ ጊዜ 1-1 ተለያይተዋል፡፡ ለመተሀራ ስኳር አንተነህ ለገሠ ሲያስቆጥር ለካፋ ቡና ተካልኝ መስፍን አስቆጥሯል፡፡
አሸናፊውን ለመለየት በተሰጡት የመለያ ምቶች ካፋ ቡና 4-2 በማሸነፍ ከፍተኛ ሊጉን የተቀላቀለ አምስተኛ ክለብ ሆኗል፡፡
10:00 ላይ ዲላ ከተማ አማራ ፖሊስን በመለያ ምት አሸንፏል፡፡ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1-1 ሲጠናቀቅ ለአማራ ፖሊስ ነፃነት ሙሉሰው ለዲላ ከተማ ማጁር ሀብቴ አስቆጥረዋል፡፡ በተሰጠው የመለያ ምትም ከፋ ቡና 9-8 አሸንፎ ከፍተኛ ሊጉን የተቀላቀለ ስድስተኛ ቡድን ሆኗል፡፡
ወደ ከፍተኛ ሊግ ያደጉ ክለቦች
አራዳ ክ/ከተማ ፣ ወልቂጤ ከተማ ፣ ለገጣፎ ከተማ ፣ ሽረ እንዳስላሴ ፣ ዲላ ከተማ ፣ ካፋ ቡና
የብሄራዊ ሊጉ የማጠቃለያ ውድድር ነገ ፍጻሜውን ሲያገኝ 04:00 ላይ ለደረጃ ሽረ እንዳስላሴ ከ ወልቂጤ ከተማ ፤ 08:00 ላይ ለዋንጫ አራዳ ክ/ከተማ ከ ለገጣፎ ከተማ ይጫወታሉ፡፡