የብሄራዊ ሊግ የማጠቃልያ ውድድር በለገጣፎ ከተማ ቻምፒዮንነት ተጠናቀቀ

የ2008 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ብሄራዊ  ሊግ ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ ለገጣፎ ከተማም ውድድሩን በቻምፒዮንነት አጠናቋል፡፡

ከሐምሌ 16 – ነሐሴ 3 በባቱ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የማጠቃለያ ውድድሩ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚና የብሄራዊ ውድድሮች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አሊሚራህ መሃመድ ፣ አቶ ዘሪሁን ቀቀቦ ፣ የለገጣፎ ከተማ ከንቲባ አቶ መስፍን አሰፉ እና የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተጠናቋል፡፡

04:00 ላይ ለደረጃ ሽረ እንዳስላሴ ወልቂጤ ከተማን 2-1 አሸነፎ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቋል፡፡ ለሽረ ሰይድ ሁሴን እና በክሪ መሀመድ ሲያስቆጥሩ የወልቂጤ ከተማን ብቸኛ ጎል እስራኤል ፍቅሩ አስቆጥሯል፡፡

08:00 ላይ በተካሄደው የፍፃሜ ጨዋታ ለገጣፎ ከተማ አራዳ ክ/ ከተማን 1-0 በማሸነፍ የውድድሩ ቻምፒዮን ሆኗል፡፡ የለገጣፎ ከተማን ወሳኝ የድል ጎል ልደቱ ለማ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡

ከጨዋታው ፍጻሜ በኋላ የሽልማት አሰጣጥ መርሃ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ ለውድድሩ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት የምስክር ወረቀት ተበርክቷል፡፡

የኮከብነት ሽልማቶች

PicsArt_1470758343355

*ኮከብ ዋና ዳኛ

ቢኒያም ወርቅአገኘው – 6000 ብር እና ዋንጫ

*ኮከብ ረዳት ዳኛ

መኮንን ብርሃኑ – 6000 ብር እና ዋንጫ

PicsArt_1470758397919

* ኮከብ ግብ ጠባቂ

ተክላይ በርኸ (ሽረ) – 10,000 ብር እና ዋንጫ

* ኮከብ ተጨዋች

ጅብሪል ናስር (አራዳ) – 10,000 ብር እና ዋንጫ

PicsArt_1470758292175

* ኮከብ አሰልጣኝ

ያሬድ ቶሌራ (ለገጣፎ) – 10,000 ብር እና ዋንጫ

* በአመቱ የዞን ውድድር 14 ጎል በማስቆጠር የአምበሪቾው ቢኒያም ጌታቸው 10,000 ተሸላሚ ሆኗል፡፡

* በየዞኑ የስፖርታዊ ጨዋነት ተሸላሚዎች

ወንጂ ስኳር ፣ ጨፌ ዶንሳ ፣ አምበሪቾ ፣ አሶሳ ከተማ ፣ ዳባት ከተማ ፣ ዋልታ ፖሊስ ፣ ቦሌ ክ/ከተማ

*የማጠቃለያ ውድድሩ የስፖርታዊ ጨዋነት አሸናፊ – አራዳ ክ/ ከተማ

* በየዞኑ አንደኛ የወጡት ክለቦች የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

PicsArt_1470758241747

* የማጠቃለያ ውድድር

3ኛ. ሽረ እንዳስላሴ (የነሐስ ሜዳልያ እና 30,000 ብር)

2ኛ. አራዳ ክፍለ ከተማ (የብር ሜዳልያ እና 40,000 ብር)

1ኛ. ለገጣፎ ከተማ (የወርቅ ሜዳልያ ፣ ዋንጫ እና 50,000 ብር)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *