የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ከግብጽ ጋር የሚያደርገውን የአፍሪካ ከ17 አመት በታች ዋንጫ የመልስ ጨዋታ በድሬዳዋ ያደርጋል፡፡
ባሳለፍነው ቅዳሜ ካይሮ ላይ ያልተጠበቀ የ3-1 ድል ያስመዘገበው የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን እሁድ ወደ አዲስ አበባ የተመለሰ ሲሆን ሰኞ እና ማክሰኞ በአአ ስታድየም ቀለል ያለ ልምምዱን አድርጓል፡፡
በትላንት እለት ወደ ድሬዳዋ ያቀናው ብሄራዊ ቡድናችን በድሬዳዋ ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን ሰመትር ሆቴል ማረፊያውን አድርጎ ለመልሱ ጨዋታ ዝግጅቱን ጀምሯል፡፡
አሰልጣኝ አጥናፉ አባተ ግብጽን ያሸነፈው ቡድን ላይ ምንም አይነት ለውጥ ሳያደርጉ ወደ ድሬደዋ ማምራታቸው ታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ እና ግብጽ ከ17 አመት በታቸ ብሄራዊ ቡድኖች ጨዋታ ነሀሴ 15 ቀን 2008 በድሬዳዋ ይካሄዳል፡፡