በአፍሪካ የክለቦች ደረጃ ከኢትዮጵያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ብቻ ተካቷል

በየዓመቱ የዓለም ክለቦች ደረጃን በማውጣት የሚታወቀው የፉትቦል ዳታ ቤዝ ድረ-ገፅ የ2016 የክለቦች ደረጃን ባሳለፍነው ሰኞ አውጥቷል፡፡

ድረ-ገፁ ከ2000 በላይ ክለቦችን በዓመታዊው ደረጃ ሲያካትት ቅዱስ ጊዮርጊስ በደረጃው ላይ የተካተተ ብቸኛው የኢትዮጵያ ክለብ ሆኗል፡፡

የአፍሪካ ክለቦች ደረጃን የበላይነት የደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ሲወስድ ኤቷል ደ ሳህል እና ኤስፔራንስ ከቱኒዚያ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ዓመቱን የደቡብ አፍሪካ አብሳ ፕሪምሺፕ ሻምፒዮን ሲሆን የካፍ ቻምፒየስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜን የተላቀለ ክለብ ነው፡፡ የዲ.ሪ. ኮንጎዎቹ ቲፒ ማዜምቤ እና ኤኤስ ቪታ ክለብ አራተኛ እና አምስተኛ ሆነዋል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአፍሪካ ክለቦች 294 ደረጃ በድህረ-ገፁ ተሰጥቶታል፡፡ በኬንያ ሰፖርትፔሳ ፕሪሚየር ሊግ ላለመውረድ እየታገለ የሚገኘው ሶፋፓካ 187ኛ ፣ የዳሬ ሰላም ሃያሎቹ  ያንግ አፍሪካንስ እና ሲምባ 325ኛ እና 348ኛ ሆነዋል፡፡

የስፔኑ ባርሴሎና ከአለም አንደኛ ሲሆን ባየር ሙኒክ፣ ሪያል ማድሪድ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ እና ጁቬንቱስ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡

ደረጃው የሚወጣው በኢሎ የደረጃ አሰጣጥ ስርዓት ሲሆን እንደፊፋ የሃገራት ደረጃ የአራት ዓመት ውጤቶችን ከግምት አያስገባም፡፡ ኢሎ የደረጃ አሰጣጥ ስርዓት ጨዋታዎች የተጠናቀቁበት የግብ ልዩነት፣ የጨዋታው ወሳኝነት፣ የሜዳ አድቫንቴጅ እና መሰል እግርኳሳዊ ጉዳዮችን ከግምት ያስገባል፡፡ ድህረ-ገፁ የሚያወጣው ደረጃ ወቅታዊ አቋምን የማያንፀባርቅ ነው የሚሉ ትችቶች ይሰነዘሩበታል፡፡

የአፍሪካ ደረጃ

1 ማሜሎዲ ሰንዳውንስ (ደቡብ አፍሪካ)

2 ኤቷል ደ ሳህል (ቱኒዚያ)

3 ኤስፔራንስ (ቱኒዚያ)

4 ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)

5 ኤኤስ ቪታ ክለብ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)

6 ኤል ሜሪክ (ሱዳን)

7 አል አሃሊ (ግብፅ)

8 አል ሂላል ኦምዱሩማን (ሱዳን)

9 ዛማሌክ (ግብፅ)

10 ኮተን ስፖርት (ካሜሮን)

.

.

294 ቅዱስ ጊዮርጊስ (ኢትዮጵያ)

Leave a Reply