​አፍሪካ በሪዮ 2016 የሴቶች እግርኳስ

የአፍሪካ ተወካዮቹ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባቡዌ በሪዮ ኦሎምፒክ የምድብ መክፈቻ ጨዋታቸውን ተሸንፈዋል፡፡ ስዊድን ደቡብ አፍሪካን 1-0 ስትረታ ሃያሏ ጀርመን ዚምባቡዌን 6-1 ረምርማለች፡፡
በምድብ አንድ የምትገኝው ደቡብ አፍሪካ በስዊድን ተሸንፋለች፡፡ በኦሎምፒኩ መክፈቻ ጨዋታ ሁለቱም ሃገራት የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ በመጀመሪያው አጋማሽ ያሳዩ ሲሆን በሁለተኛው አጋማሽ ስዊድን የተሻለ ነበረች፡፡ የደቡብ አፍሪካዋ ግብ ጠባቂ ሮክን ባርከር የሰራችውን ስህተት ተጠቅማ ፊሸር የስዊድንን የማሸነፊያ ግብ አስቆጥራለች፡፡ በምድብ ሌላ ጨዋታ አዘጋጇ ብራዚል ቻይናን 3-0 በማሸነፍ የምድቡ መሪ ሆናለች፡፡

በሴቶች እግርኳስ እምብዛም ስም የሌላት ዚምባቡዌ በጀርመን በጨዋታ ብልጫ 6-1 በሆነ ሰፊ ውጤት ኦሎምፒኩን ጀምራለች፡፡ የዳዊት እና ጎልያድ ጨዋታ ተብሎ በተሰየመው በዚህ ጨዋታ ዚምባቡዌ የጀርመኖችን ከፍተኛ ጫና መቋቋም ተስኗቸው ተይቷል፡፡ ካዱካዋሺ ባሶፖ የዚምባቡዌን ማስተዛዘኛ ግብ በሁለተኛው አጋማሽ አስቆጥራለች፡፡ በምድቡ ሌላ ጨዋታ አብዛኛው የጨዋታ ክፍለግዜ በ10 ተጫዋች መጫወት የተገደደችው ካናዳ አውስትራሊያን 2-0 አሸንፋለች፡፡ ምድብ ሁለትን ጀርመን ትመራለች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *