‹‹ በቡድኔ ውጤት ደስተኛ ነኝ ›› ንጉሴ ደስታ

በቻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታ እሁድ እለት የዛንዚባሩን ኬኤምኬኤም 3-0 ባሸነፈው ቡድናቸው አቋም ደስተኛ መሆናቸውን አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ ተናግረዋል፡፡

‹‹ ይህንን ጨዋታ ያደረግነው ለረጅም ጊዜያት በውድድር ውስጥ ሳንሆን በመሆኑ በቡድኑ የሜዳ ላይ አቋም ረክቻለሁ፡፡ ቡድኑ በርካታ የግብ እድሎችን መጠቀም ባይችልም ይህንን ድክመት በሂደት በማረም መልካም ጉዞ ለማድረግ ተዘጋጅተናል፡፡››

‹‹ ደደቢት በጨዋታው የነበረው ጠንካራ ጎን እንደ ቡድን መንቀሳቀሱ እና ወደ ግብ ቶሎ ቶሎ ለመድረስ መቻሉ ነው፡፡ ለክለቡም የመጀመርያ የቻምዮንስ ሊግ ጨዋታ እንደመሆኑ በተጨዋቾቼ ላይ የነበረው መንፈስ ልዩ ነበር ›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

{jcomments on}

ያጋሩ