ኮንፌድሬሽን ካፕ፡ ኤቷል ደ ሳህል እና ፉስ ራባት ወደ ግማሽ ፍፃሜ ለመግባት ይጫወታሉ

የኦሬንጅ ካፍ ኮንፌድሬሽን ካፕ የምድብ አምስተኛ መርሃ ግብር ዛሬ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራሉ፡፡ በምድብ ሁለት የሚገኙት ፉስ ራባት እና ኤቷል ደ ሳህል ወደ ግማሽ ፍፃሜው የሚወስዳቸውን ትኬት ለመቁረጥ ተጋጣሚዎቻቸውን ማሸነፍ በቂያቸው ነው፡፡

ፉስ ራባት ወደ ግማሽ ፍፃሜ ለማለፍ አል አሃሊ ትሪፖሊን ማሸነፍ በቂው ነው፡፡ ፉስ ምድብ ሁለትን በ10 ነጥብ የሚመራ ሲሆን ከተከታዩ ኤቷል ደ ሳህል በሶስት ነጥብ ይርቃል፡፡ አሃሊ ትሪፖሊ ከምድቡ ከወዲሁ በመሰናበቱ ጨዋታው ለሊቢያው ክለብ ትርጉም የለውም፡፡

ኤቷል ደ ሳህል ካውካብ ማራካሽን ሶስ ላይ የሚያስተናግድበት ጨዋታም ተጠባቂ ነው፡፡ ካውካብ በስድስት ነጥብ ሶስተኛ ሲሆን በኤቷል የሚሸነፍ ከሆነ ከምድቡ ተሰናባች ይሆናል፡፡ በመጀመሪያው ጨዋታ ካውካብ 2-1 ማሸነፍ ችሏል፡፡

ዓርብ ነሃሴ 6/2008

18፡30 – አል አሃሊ ትሪፖሊ (ሊቢያ) ከ ፉት ዩኒየን ስፖርት ራባት (ሞሮኮ)

21፡00 – ኤቷል ስፖርቲቭ ደ ሳህል (ቱኒዚያ) ከ ካውካብ አትሌቲክ ክለብ ማራካሽ (ሞሮኮ) (ስታደ ኦሎምፒክ ደ ሶስ)

Leave a Reply