ቻምፒየንስ ሊግ፡ አል አሃሊ እና ዜስኮ ዛሬ ይጫወታሉ

በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ አምስተኛ ጨዋታ አል አሃሊ ዜስኮ ዩናይትድን ሱዌዝ ላይ ያስተናግዳል፡፡ በምድብ አንድ የሚገኙት ሁለቱ ክለቦች መካከል የሶስት ነጥብ ልዩነት አለ፡፡

አል አሃሊ ባሰለፍነው ሰኞ በግብፅ ዋንጫ ፍፃሜ በተቀናቃኙ ዛማሌክ 3-1 ተሸንፎ ዋንጫ ያጣ ሲሆን ዜስኮ በዛምቢያ ኤምቲኤን ፕሪምየር ሊግ በውድድር ዓመቱ የተሳካ ጉዞ እያደረገ አይደለም፡፡

በቻምፒየንስ ሊጉ በሜዳው አንድም የምድብ ጨዋታ ማሸነፍ ያልቻለው አል አሃሊ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ለማለፍ ማሸነፍን መሰረት አድርጎ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡ ዜስኮ በሜዳው እና ከሜዳው ውጪ የማሸነፍ ሪከርዱ የተለያየ ሲሆን አሃሊን ማሸነፍ ከቻለ አንድ እግሩን ወደ ግማሽ ፍፃሜው ያስገባል፡፡

ዓርብ ነሃሴ 6/2008


21፡30 – አል አሃሊ (ግብፅ) ከ ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ) (ሱዌዝ አርሚ ስታዲየም)

Leave a Reply