መሰረት ማኒ ለኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ተመረጡ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በመስከረም ወር 2009 ለሚጀመረው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ዝግጅት አሰልጣኝ መሰረት ማኒን ለመሾም ከውሳኔ ላይ መድረሱ ታውቋል፡፡

ከወራት በፊት ከድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝነታቸው የተነሱት አሰልጣኝ መሰረት ማኒ ከዩናይትድ ስቴትስ የተመለሱ ሲሆን ለሉሲዎቹ ሃላፊነት ከፌዴሬሽኑ ጋር በቃል ደረጃ ከስምምነት ደርሰዋል፡፡ በቀጣዮቹ ቀናትም ውል ተፈራርመው በይፋ የሉሲዎቹ አሰልጣኝ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ለመጀመርያ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን ከመስከረም 1 እስከ 14 ቀን 2009 በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ይካሄዳል፡፡

Leave a Reply