በዝውውር መስኮቱ ባለፉት ጥቂት ቀናት የተካሄዱ የዝውውር እንቅስቃሴዎችን ከዚህ በታች ባለው መልኩ አቅርበንላችኋል 

16148

ሲዳማ ቡና

ሲዳማ ቡና የሀዋሳ ከተማውን ተከላካይ ግሩም አሰፋ እና የአርባምንጩ አጥቂ አብይ በየነን ያስፈረመ ሲሆን የተካልኝ ደጀኔን ፊርማ በአርባምንጭ ተቀድሞ ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ ሲዳማ ቡና ከተስፋ ቡድኑ ሦስት ተጫዋቾችን ወደ ዋናው ቡድን አሳድጓል፡፡


13235

ወላይታ ድቻ

2 ተጫዋቾች ከብሄራዊ ሊግ ያስፈረመው ወላይታ ድቻ አሁን ደግሞ ፊቱን ወደ ከፍተኛ ሊግ በነገሌ ቦረና ድንቅ የውድድር ዘመን ያሳለፈው ዳግም በቀለን ለሁለት አመት አስፈርሟል፡፡ አጥቂው ዳግም በዚህ የውድድር ዘመን በአመዛኙ የነገሌ ቦረና ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርጓል፡፡  አሰልጣኝ መሳይ የአማካይ ክፍላቸውን ለማጠናከር ከከፍተኛ ሊግ ተጨማሪ ተጨዋች በቅርቡ ሊያስፈርሙ እንደሚችሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡


16135

ኢትዮዽያ ቡና

የአምበሉን የመስኡድ መሃመድን ውል ያደሰው ኢትዮዽያ ቡና በባቱ ከተማ ሲካሄድ ከሰነበተው የብሄራዊ ሊግ ማጠቃለያ ውድድር ላይ ተጫዋቾች ለመመልመል የቴክኒክ ሀላፊው ፣ የቡድን መሪውና የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኙን ወደ ስፍራው መላኩ የሚታወስ ሲሆን ግዮን መላኩ እና መልካሙ ሲሳይ የተባሉ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቾችን ማስፈረሙን ለማወቅ ችለናል፡፡


13243-1

ሀዋሳ ከተማ

የቀድሞው የአዳማ ከተማ እና ንግድ ባንክ አጥቂ አብይ ሞገስ ማረፊያውን ሀዋሳ ከተማ አድርጓል፡፡ ሀዋሳ ከክለቡ በተሰናበቱት ዮሃንስ በዛብህ እና ተመስገን ተክሌ ምትክ ቶጎዋዊ ግብ ጠባቂ እና ጋናዊ አጥቂ ለማምጣት ጥረት እያደረገ እንደሆነም ታውቋል፡፡


16147

አርባምንጭ ከተማ

አርባምንጭ ደደቢን የለቀቀው ተካልኝ ደጀኔ እና የአዳማ ከተማው አማካይ ወንድሜነህ ዘሪሁንን የግሉ አድርጓል፡፡ አምበሉ አማኑኤል ጎበና ውሉን ያደሰ ሲሆን ታደለ መንገሻ ፣ እንዳለ ከበደ እና ቢያድግልኝ ኤልያስ ያቀረቡት ጥያቄ መልካም መልስ እንዳገኘ እና የክለቡ አመራር ሀዋሳ ድረስ በመምጣት የተደራደሩ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በቅርቡም ፊርማቸውን ያኖራሉ ተብሏል፡፡


16132

ኢትዮዽያ ንግድ ባንክ

ኢትዮዽያ ንግድ ባንክ ግዙፉ አጥቂ ፒተር ኑዋዲኬን ለአንድ አመት ውል አስፈርሟል፡፡ አሰልጣኝ ፀጋዬ ሁነኛ የመስመር አጥቂ ለማስፈረም ጥረት እያደረጉ እንደሆነም ታውቋል፡፡

ከክለቡ ጋር በተያያዘ ዜና በውድድር አመቱ ብዙም ግልጋሎት ያልሰጠው አጥቂው ቢኒያም አሰፋ ከክለቡ ጋር የመቆየቱ ነገር አጠራጣሪ ሲሆን ወደ ጅማ አባቡና ለማምራት ድርድር እንደጀመረ ታውቋል፡፡


PicsArt_1471109828822

አዲስ አበባ ከተማ

ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደገው አአ ከተማ ራሱን አጠናክሮ በሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ የአማካይና አጥቂ ስፍራ ተጫዋቾትን ከኬንያ ፤ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ደግሞ ከጋና ለማምጣት ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ የከፍተኛ ሊጉ ክለቦች በተለይም ዳሽን ቢራ የአአ ከተማ የዝውውር ራዳር አርፎባቸዋል፡፡


16133

መከላከያ

የተሻ ግዛውን ከዳሽን ያስፈረመው መከላከያ ሌላውን የዳሽን የመስመር አጥቂ መስፍን ኪዳኔን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል፡፡ ተመስገን ገብረጻድቅን ከሀዲያ ሆሳእና ማስፈረም የቻለው ጦሩ ተጨማሪ ተጨዋቾችን ወደ ክለቡ ለማምጣት ድርድር ላይ እንደሆነም የክለቡ አሰልጣኝ ምንያምር ጸጋዬ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡


16149

ደደቢት

አመቱን በወላይታ ድቻ ያሳለፈው ሰለሞን ሀብቴ ወደ ደደቢት ተመልሷል፡፡ ሰማያዊዎቹ የዳሽን ቢራው ተከላካይ ያሬድ ባየህን ለማስፈረም ከጫፍ እንደደረሰም ለክለቡ ቅርበት ካላቸው ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ደደቢት በቅርቡ ያስፈረማቸውን ተጫዋቾች በይፋ እንደሚያስተዋውቅም ታውቋል፡፡


16134

ኤሌክትሪክ

ከመውረድ ለጥቂት የተረፈው ኢትዮ ኤሌክትሪክ አሰልጣኝ ብርሃኑ ባዩ በቀጣዩ አመት ተጠናክሮ ለመቅረብ የ2009 እቅዳቸውን ለክለቡ ቦርድ ቢያቀርቡም በቶሎ ምላሽ ባለማግኘታቸው ተጫዋቾች ማስፈረም አልቻሉም፡፡

ያም ሆኖ ከከፍተኛ ሊግ ተጫዋቾችን ለማስፈረም እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡


24715

ፋሲል ከተማ

ዘንድሮ ወደ ሊጉ ማደጉን ቀድሞ ያረጋገጠው ፋሲል ከተማ ተጫዋቾች ለማስፈረም እንቅስቃሴ እያደረገ ቢገኝም እስካሁን አንድም ተጫዋች በእጁ ማስገባት አልቻለም፡፡

ሆኖም ክለቡን ለማፍረስ የተቃረበው ዳሽን ቢራ ፋሲል ከተማን በከፍተኛ ገንዘብ ስፖንሰር ለማድረግ እና ውላቸውን ያላጠናቀቁ ተጫዋቾችን ለፋሲል ለመስጠት እንዳሰበ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡


* ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ አዳማ ከተማ ፣ ወልድያ ፣ ድሬዳዋ ከተማ ፣ ወልድያ እና ጅማ አባ ቡና ባለፉት ቀናት ይህ ነው የሚባል አዲስ የዝውውር እንቅስቃሴ አላደረጉም፡፡

1 Comment

Leave a Reply