ኮንፌድሬሽን ካፕ፡ ያንጋ የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቧል

የታንዛኒው ያንግ አፍሪካንስ ዳሬ ሰላም ላይ ኤምኦ ቤጃያን 1-0 ማሸነፍ ችሏል፡፡ በምድብ አራት የሚገኘው ያንጋ የመጀመሪያ ድሉን ሲያስመዘግብ ቤጃያ ወደ ግማሽ ፍፃሜ የማለፉን ነገር አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል፡፡

ኢትዮጵያዊው ባምላክ ተሰማ በመራው ጨዋታ ያንጋ በእንቅስቃሴ ተሽሎ የታየ ሲሆን ብዙ ግብ መሆን የሚገባቸውን ዕድሎች በታንዛኒያው ክለብ ሲመክኑ ተስተውሏል፡፡ የያንጋን ብቸኛ የድል ግብ ከመረብ ያሳረፈኽ ቡሩንዲያዊው አሚሲ ታምቤዌ ነው፡፡

PicsArt_1471162467358

በኮንፌድሬሽን ካፑ የምድብ ጨዋታ አንድ ግብ ብቻ ያስቆጠረው የአልጄሪያው ክለብ በመጀመሪያው አጋማሽ ኢላማውን የጠበቀ አንድም የግብ ሙከራ አላደረገም፡፡

ውጤቱ ያንጋን አሁንም ወደ ግማሽ ፍፃሜው የማለፍ ተስፋው እንዳይሟጠጥ አድርጓል፡፡

በምድቡ ሌላ ጨዋታ ዛሬ ሚዲአማ ቲፒ ማዜምቤን ያስተናግዳል፡፡ የቤጃያ መሸነፍ ለጋናው ክለብ ጥሩ ዜና ሲሆን የምድቡ መሪ ማዜምቤን ወደ ግማሽ ፍፃሜው አሳልፎታል፡፡ ሚዲአማ ጨዋታውን ማሸነፍ ከቻለ ከቤጃያ እና ያንጋ ወደ ግማሽ ፍፃሜ የማለፍ የተሻለ ዕድል ይኖረዋል፡፡

 

የቅዳሜ ጨዋታ

ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ) 1-0 ሞሊዲያ ኦሎምፒክ ቤጃያ (አልጄሪያ)

የዛሬ ጨዋታ

15፡00 – ሚዲአማ (ጋና) ከ ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) (ኢሲፖንግ ስፖርት ስታዲየም)

የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ

21፡00 – ዋይዳድ አትሌቲክ ክለብ (ሞሮኮ) ከ አሴክ ሚሞሳስ (ኮትዲቯር) (ኮምፕሌክስ ፕሪንስ ሞላይ አብደላ ስታዲየም)

Leave a Reply