ወደ ብሄራዊ ሊግ የሚያድጉ ክለቦችን ለመለየት በአርባምንጭ ከተማ አስተናጋጅነት ከሐምሌ 21 – ነሐሴ 8 ሲካሄድ የቆየው የኢትዮዽያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡
በመዝጊያ ስነስርአቱም የጋሞ ጎፋ ዞን ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ አባተ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ቾል ቤል ፣ የተጂ ከተማ ከንቲባ ታምሩ ካህሳይ የቢሸፍት አውቶሞቲቭ ም/ ስራ አስኪያጅ ኮ/ል ሄዶ ሻኮ ተገኝተዋል፡፡
03:00 ላይ በተደረገው የደረጃ ጨዋታ ሀዲያ ሊሞ ከ ጨንቻ ከተማ በመደበኛው ክፍለ ጊዜ ያለግብ አገባደው በተሰጡት የመለያ ምቶች ሀዲያ ሊሞ 5 – 3 በማሸነፍ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡
09:00 ላይ በተካሄደው የፍፃሜ ጨዋታ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ተጂ ከተማን ከፍፁም የጨዋታ ብልጫ ጋር 3-0 በማሸነፍ የውድድሩ ቻምፒዮን ሆኗል፡፡
ከጨዋታው ፍፃሜ በኋላ የሽልማት መርሐ ግብር ቀጥሏል፡፡
የኮከቦች ሽልማት
ኮከብ ዋና ዳኛ
ብርሃኑ መኩሪያ – 3000 ብር እና ዋንጫ
ኮከብ ረዳት ዳኛ
ለአለም ዋሲሁን – 3000 ብር እና ዋንጫ
ኮከብ ተጨዋች
አስፕሬ መሀመድ (ሀዲያ ሊሞ) – 5000 ብር እና ዋንጫ
ኮከብ ግብ ጠባቂ
ንጉሴ ሙልጌታ (ጨንቻ ከተማ) – 5000 ብር እና ዋንጫ
ኮከብ ጎል አስቆጣሪ
ኢሳያስ ብርሃኔ (ቢሸፍቱ አ.) እና ማቲዮስ ኤልያስ (ጨንቻ ከተማ) በ5 ግቦች – ዋንጫ እና 2500 ብር ለእያንዳንዳቸው
ኮከብ አሰልጣኝ
ግዛው ልኬ (ቢሸፍቱ) – 5000 ብር እና ዋንጫ
የስፖርታዊ ጨዋነት ዋንጫ – ቢሸፍቱ አ.
የደረጃ ሽልማቶች
1ኛ. ቢሸፍቱ አውቶሞቲቭ – 30,000 ብር ፣ የወርቅ ሜዳልያ እና ዋንጫ
2ኛ. ተጂ ከተማ – 25,000 ብር እና የብር ሜዳልያ
3ኛ. ሀዲያ ሊሞ – 15,000 ብር እና የነሐስ ሜዳልያ
በ8 ምድብ ተከፍሎ በ35 ክለቦች መካከል ሲካሄድ ከሰነበተው የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና 8 ክለቦች ወደ 2009 ብሄራዊ ሊግ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ወደ ብሄራዊ ሊግ ያለፉ ክለቦች
1 ወለንጪቲ
2 ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ
3 ለገጣፎ ከተማ ቢ
4 ጨንቻ ከተማ
5 ራያ ከተማ
6 ተጂ ከተማ
7 ሀዲያ ሊሞ
8 ገላን ከተማ