ቻምፒየንስ ሊግ፡ ዋይዳድ ካዛብላንካ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፏል

የሞሮኮው ዋይዳድ ካዛብላንካ አሴክ ሚሞሳስን 2-1 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፉን አረጋግጧል፡፡ አሴክ ሚሞሳስ ከምድብ አንድ መሰናበቱን ሲያረጋግጥ አል አሃሊን ይባስ ጫና ውስጥ ከቶታል፡፡

ዕሁድ ምሽት በተደረገው ጨዋታ ኤሴክ ሚሞሳስ ከምድብ ላለመሰናበት አንድ ነጥብ ቢያስፈልገውም በአብደላዲም ካድሮፍ ግብ ተመርተዋል፡፡ ክራሂር ዛካሪ አሴክን አቻ ማድረግ ቢችልም የኮንጎ ብራዛቪል ኢንተርናሽናሉ ፋብሪስ ኦንዳማ የዋይዳድን ማሸነፊያ ግብ ከመረብ አዋህዷል፡፡ ውጤቱ ዋይዳድን በ10 ነጥብ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ሲያሳልፍ አሴክ ሚሞሳስ በ4 ነጥብ መውደቁን አረጋግጧል፡፡ ዜስኮ ዩናይትድ ዋይዳድን ተከትሎ የማለፍ ተስፋው ከአል አሃሊ እጅጉን የተሻለ ሆኗል፡፡

ቻምፒየንስ ሊጉ ዛሬ ሲቀጥል በምድብ ሁለት ዛማሌክ እና ኢኒምባ ይገናኛሉ፡፡ ዛማሌክ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ አቻ በቂው ሲሆን የናይጄሪያው ኢኒምባ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ለማለፍ ጨዋታውን ማሸነፍ አለበት፡፡ ዛማሌክ ባሳለፍነው ሳምንት የግብፅ ዋንጫን ቀንደኛ ተቀናቃኙ አል አሃሊን 3-1 በማሸነፍ ያነሳ ሲሆን ኢኒምባን የማሸነፍ የተሻለ ግምት ተሰጥቶታል፡፡

 

የዕሁድ ውጤት፡

ዋይዳድ አትሌቲክ ክለብ (ሞሮኮ) 2-1 አሴክ ሚሞሳስ (ኮትዲቫር)

የዛሬ ጨዋታ

ዛማሌክ (ግብፅ) ከ ኢኒምባ ኢንተርናሽናል (ናይጄሪያ) (ፔትሮ ስፖርት ስታዲየም)

Leave a Reply