ኮንፌድሬሽን ካፕ፡ ሚዲአማ ቲፒ ማዜምቤን አሸንፏል

በካፍ ኮንፌድሬሽን ካፕ ሚዲአማ ሺኮንዲ ላይ ቲፒ ማዜምቤን 3-2 አሸንፎ ወደ ግማሽ ፍፃሜ የማለፍ ተስፋውን አለምልሟል፡፡

በምድብ አንድ ከሚገኙት የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ወሳኝነቱ ለሚዲአማ የነበረ ሲሆን በጨዋታው ከፍተኛ ፉክክር ታይቷል፡፡

ቲፒ ማዜምቤ አስቀድሞ ማለፉን በማረጋገጡ ሚዲአማ ጨዋታውን የማሸነፍ ጫና ነበረበት፡፡ ሚዲአማ በኢኖች አታ አጊ እና ሞሰስ ሳርፖን (ፍፁም ቅጣት ምት) ግቦች 2-0 መምራት ቢችልም የአምስት ጊዜ የአፍሪካ ሻምፒዮኑ ማዜምቤ በጆናታን ቦሊንጊ እና ሬንፎርድ ካላባ ግቦች 2 አቻ መሆን ችሏል፡፡ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሁለት ደቂቃዎች ሲቀሩት ክዌሲ ዶንሱ የሚዲአማን ወሳኝ ግብ ከመረብ አዋህዷል፡፡

ውጤቱ የሚዲአማን የግማሽ ፍፃሜ መንገድ ሲያመቻች የምስራቅ አፍሪካ ተወካዩን ያንግ አፍሪካንስን ከምድብ አሰናብቷል፡፡

 

የዕሁድ ውጤት

ሚዲአማ (ጋና) 3-2 ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)

Leave a Reply