የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የ2009 የውድድር ዘመን ፕሪሚየር ሊግ የሚጀመርበትን ቀን ይፋ አድርጓል፡፡
ፌዴሬሽኑ ባስታወቀው መሰረት መስከረም 29 ቀን 2009 አዲሱ የውድድር ዘመን ይጀመራል ተብሏል፡፡
ክለቦች ለአዲሱ የውድድር ዘመን የሚያካሂዱትን ምዘገባ አስከ ነሀሴ 20 እንዲያጠናቅቁ ገደብ የተሰጣቸው ሲሆን የአመቱን የታዛቢዎች እና የዳኞችን ክፍያ እስከ ነሀሴ 25 እንዲያጠናቅቁ ቀነ ገደብ ተሰጥቷል፡፡ የተጫዋቾች ምዝገባ እና የውል ምዝገባ ማጠናቀቂያ ደግሞ እስከ መስከረም 29 እንዲያጠናቅቁ ገደብ ተሰጥቷል፡፡
መስከረም 5 ቀን 2009 የሊጉ መርሃ ግብር እጣ የሚወጣ ሲሆን መስከረም 29 ይጀመራል፡፡
የ2009 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ16 ክለቦች መካከል ይካሄዳል፡፡ አንዳንድ የሊጉ ክለቦችም ከዚህ ሳምንት ጀምሮ የቅድመ ውድድር ዝግጅት ማድረግ ጀምረዋል፡፡
በዛሬው እለት ደደቢት ፌዴሬሽኑ የፕሪሚየር ሊጉ መጀመርያ ቀንን እንዲያሳውቅ የሚጠይቅ መግለጫ ማውጣቱ የሚታወስ ሲሆን ከፌዴሬሽኑ ባገኘነው መረጃ መሰረት የሊጉ መጀመርያ ቀንን ለመወሰን በቅድሚያ እንደታሰበበትና የደደቢትን መግለጫ ተከትሎ ይፋ እንዳልተደረገ ተነግሯል፡፡