‹‹ ምርጡ ብቃቱ ላይ ገና አልደረስኩም ›› ሽመክት ጉግሳ

በእሁዱ የደደቢት እና ኬኤምኬኤም ጨዋታ ግብ ከማስቆጠር በተጨማሪ ኮከብ ሆኖ የዋለው የመስመር አማካዩ ሸመክት ጉግሳ ከሃት-ትሪክ ጋዜጣ ጋር ባደረገው አጭር ቆይታ በመጀመርያ ኢንተርናሽናል ጨዋታ ባሳየው አቋም ደስተኛ እንደሆነ ገለጧል፡፡

‹‹የደደቢት የእሁድ ድል ላይ ዋን ተዋይ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ፡፡ ጥሩ ከመንቀሳቀሴ ባሸገር አንድ ግብ ማስቄጠሬም ደስታን ፈጥሮልኛል፡፡ ያም ሆኖ በጨዋታው ያባከንኳት ግልፅ ሳስባት ግርምትን ፈጥራብኛለች፡፡ በቀጣይ ጨዋታዎች እንዲህ አይነት ስህተት ላለመስራት ጥረት አደርጋለሁ››

ከሀዋሳ ከነማ ደደቢትን ዘንድሮ የተቀላቀለው ሽመክት ጉግሳ የምንያህል ተሸመ እና በኃይሉ አሰፋን መልቀቅ ተከትሎ በቶሎ የቋሚነት እድልን ያገኘ ሲሆን ከወዲሁ በፈጣን ሩጫ የተጀበ ድንቅ እንቅስቃሴ በማድረግ አሰልጣኙን አሳምኗል፡፡ ፈጣኑ የመስመር አማካይ ግን ጋና ከዚህም በላይ እሻሻላለሁ ይላል፡፡

‹‹ በደደቢት እስካሁን ሙሉ አቋሜን አሳይቻለሁ ብዬ አላስብም፡፡ በሀዋሳ የነበረኝን ድንቅ አቋም በደደቢት እንደምደግመው አምናለሁ፡፡››

{jcomments on}

ያጋሩ