የሉሲዎቹ አሰልጣኝ መሰረት ማኒ ለ31 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው የተሾሙት መሰረት ማኒ በመስከረም ወር ለሚደረገው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ዝግጅት ለ31 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል፡፡

ጥሪ ከተደረገላቸው መካከል ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 10 ተጫዋቾችን በማስመረጥ ቀዳሚ ሲሆን ደደቢት 6 ፣ መከላከያ 5 ተጫዋቾችን አስመርጠዋል፡፡

ሉሲዎቹ ነገ በኢትዮጵያ ሆቴል ተሰባስበው አርብ ወደ ድሬዳዋ በማቅናት ዝግጅት የሚጀምሩ ሲሆን የኢትዮጵያ ቡና ረዳት አሰልጣኝ የሆነችው እየሩሳሌም ነጋሽ እና የመከላከያ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ተረፈ ጉደታ የመሰረት ማኒ ረዳት ሆነው ተሹመዋል፡፡


ግብ ጠባቂዎች

ሊያ ሽብሩ (ደደቢት) ፣ ማርታ በቀለ (መከላከያ) ፣ ታሪኳ በርገና (ድሬዳዋ ከተማ) ፣ ገነት አክሊሉ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ብዙዬ ታደሰ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

ተከላካዮች

አትክልት አሸናፊ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ መስከረም ካንኮ (ደደቢት) ፣ ምህረት መለሰ (መከላከያ) ፣ ጥሩአንቺ መንገሻ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ፅዮን እስጢፋኖስ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ እፀገነት ብዙነህ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ሀብታም እሸቱ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ አሳቤ ሙሶ (ዳሽን ቢራ) ፣ አረጋሽ ፀጋ (ሲዳማ ቡና) ፣ ገነት ሃይሉ (አዳማ ከተማ)

አማካዮች

እመቤት አዲሱ (መከላከያ) ፣ ኤደን ሽፈራው (ደደቢት) ፣ ሰናይት ቦጋለ (ደደቢት) ፣ ብርቱካን ገብረክርስቶስ (ደደቢት) ፣ ፍቅርተ ብርሃኑ (መከላከያ) ፣ ብሩክታዊት ግርማ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ህይወት ደንጊሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ሰርካለም ቦጋለ (ዳሽን ቢራ) ፣ ትዕግስት ዘውዴ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ አዲስ ንጉሴ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ቅድስት ቦጋለ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)

አጥቂዎች

ሎዛ አበራ (ደደቢት) ፣ ምስር ኢብራሂም (መከላከያ) ፣ ረሂማ ዘርጋ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ሽታዬ ሲሳይ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) መዲና አወል (ቅድስት ማርያም ዩ.)

1 Comment

  1. If Dinkinesh Bekele (Lucy) From DDFC will be considered in the defense part, the team will have been better.

Leave a Reply