ብሄራዊ ቡድኑ በሀዋሳ ዝግጅቱን ሲቀጥል አቤል ማሞ ጉዳት አጋጥሞታል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በነሀሴ መጨረሻ ከሲሸልስ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ዝግጅቱን በሀዋሳ ቀጥሏል፡፡

የአሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይሌ ስብስብ በግል ጉዳይ ከቡድኑ ውጪ ከሆነው ተስፋዬ አለባቸው እና ከውጪ ሃገራት ክለቦች የተመረጡች ሽመልስ እና ዋሊድ በቀር ዝግጅት ማድረጉን ቀጥሏል፡፡

ዛሬ ጠዋት በነበረው የልምምድ መርሃ ግብር አቤል ማሞ ግራ እጁ ላይ የስብራት ጉዳት አጋጥሞታል፡፡ አቤል እጁ ላይ ብሎን የገባለት ሲሆን የጉዳቱ መጠን ከበድ ያለ በመሆኑ ከብሄራዊ ቡድኑ ውጭ እንዳያደርገው ተሰግቷል፡፡

አቤል ከሌሶቶ ጋር ለነበረው ጨዋታ ዝግጅት መከላከያ ሜዳ ላይ በነበረው ልምምድ ላይ እጁ ላይ መጠነኛ ጉዳት አጋጥሞት እንደነበረ ይታወሳል፡፡

ከአቤል ማሞ በተጨማሪ አብዱልከሪም መሃመድ መጠነኛ መጠነኛ ጉዳት አጋጥሞት ልምምዱን ያቋረጠ ሲሆን አመሻሽ ላይ በተካሄደው ሁለተኛ ልምምድ ላይ ሳይሳተፍ ቀርቷል፡፡

ጌታነህ ከበደ ከሰኞ ጀምሮ ከቡድኑ ጋር ተቀላቅሎ ልምምዱን የጀመረ ሲሆን ሽመልስ በቀለ እና ዋሊድ አታ እስካሁን ቡድኑን አልተቀለቀሉም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *