የግብፅ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ድሬዳዋ ገብቷል

በ2017 ማዳጋስካር ለምታስተናግደው ከ17 አመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ ኢትዮጵያ ግብፅን ድሬዳዋ ላይ ታስተናግዳለች፡፡

የግብጽ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን 31 የልኡካን ቡድን በመያዝ ማለዳ ድሬደዋ የደረሰ ሲሆን በድሬዳዋ አስተዳደር ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ ዛሬ አመሻሽ ላይም ቀለል ያለ ልምምዱን ሰርቷል፡፡

ግብፅ በመጀመርያው ጨዋታ ካይሮ ላይ የደረሰባትን አስደንጋጭ የ3-1 ሽንፈት ለመቀልበስ አልማ ወደ ሜዳ ትገባለች፡፡

PicsArt_1471624936580

የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የሁለቱንም ቡድኖች የልዑካን ቡድን የእንኳን ደህና መጣቹ  የእራት ግብዣ በራስ ሆቴል አመሻሹ ላይ አዘጋጅቷል፡፡

PicsArt_1471625687417

በተያያዘ የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ለእሁዱ ጨዋታ ልምምዱን ሲቀጥል ቋሚ ተሰላፊዎችን በመለየት የመከላከልና የማጥቃት ልምምዶችን ሰርተዋል፡፡ ከጉዳት ጋር በተያያዘ ሁሉም በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙም ታውቋል፡፡

ጨዋታውን የሚመሩት የሱዳን ዳኞች
ጨዋታውን የሚመሩት የሱዳን ዳኞች

በእሁዱ ጨዋታ ዙርያ የሁለቱንም ቡድኖች አሰልጣኞችና ተጨዋቾች ለሶከር ኢትዮዽያ የሰጡትን አስተያየት ነገ ይዘን የምንቀርብ መሆኑን ከወዲሁ እንገልፃለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *