የመልሱ ጨዋታ ከባድ ይሆናል ›› ገብረመድህን ኃይሌ

ትላንት በኮንፌድሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ በሊዮፓርድስ 2-0 የተረቱት የመከላከያው አሰልጣኝ ገብረ መድን ኃይሌ በመልሱ ጨዋታ ለማሸነፍ ያላቸውን እንደሚሰጡ ገልፀዋል፡፡

‹‹ የመልሱ ጨዋታ በጣም ከባድ ይሆንብናል፡፡ እሁድ በምናደርገው ጨዋታ በቅብብሎች የሊዮፓርድስን የተከላካይ መስመር ለማስከፈት እንሞክራለን፡፡ ብዙ እድሎችን መፍጠር ላይ ማተኮር አለብን ፡፡ በአጠቃላይ የግብ እድሎችን በመጨረስ በኩል ጠንክረን መስራት ይኖርብናል፡፡ ›› ሲሉ ከጨዋታው በኃላ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋቸውን በመጪው እሁድ የሚያደርጉ ሲሆን በድምር ውጤት አሸንፎ የሚያልፈው ክለብ በአንደኛው ዙር የደቡብ አፍሪካው ሱፐርስፖርት ዩናይትድ እና የቦትስዋናው ጋቦሮኔ ዩናይትድ አሸናፊን ይገጥማል፡፡

{jcomments on}