የኮፓ ኮካ ኮላ ከ15 አመት በታች ማጠቃለያ ውድድር ዛሬ ተጀመረ

ኮካ ኮላ ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው የኮፓ ኮካ ኮላ ከ15 አመት በታች የማጠቃለያ ውድድር ዛሬ ተጀምሯል፡፡

ከነሀሴ 20 እስከ ጳጉሜ 1 ቀን 2008 በቢሾፍቱ ከተማ የሚደረገው ውድድር የእጣ ማውጣት ስነ ስርአት ዛሬ ጠዋት የተካሄደ ሲሆን በውድድሩ ሒደት ዙርያ ውይይትም ተደርጓል፡፡

PicsArt_1472224886348

በሁለቱም ፆታ የተደረገው ድልድል ይህን ይመስላል፡፡


ወንዶች

ምድብ ሀ

አዲስ አበባ ፣ ድሬዳዋ ፣ ኦሮምያ ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ

ምድብ ለ

ሀረሪ ፣ አማራ ፣ ኢትዮ ሶማሌ

ምድብ ሐ

አፋር ፣ ጋምቤላ ፣ ደቡብ


ሴቶች

ምድብ ሀ

ኢትዮ ሶማሌ ፣ ኦሮምያ ፣ ደቡብ ፣ አፋር

ምድብ ለ

ጋምቤላ ፣ ሐረሪ ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ

ምድብ ሐ

ድሬዳዋ ፣ አዲስ አበባ ፣ አማራ


ከየምድባቸው 1 ደረጃ ያገኙ ክልሎች ወደ ግማሽ ፍጻሜ ሲያልፉ በጥሩ 2ኝነት የሚያጠናቅቅ አንድ ክልል ግማሽ ፍጻሜውን ይቀላቀላል፡፡

የማጠቃለያ ውድድሩ ይፋዊ የመክፈቻ ስነ ስርአት ነገ የሚደረግ ሲሆን ዛሬ የሴቶች ውድድሮች ተጀምረዋል፡፡

PicsArt_1472224794462

07:30 ለምለም ተስፋ ሜዳ ላይ ጋምቤላ ከ ሐረር ያደረጉት ጨዋታ በጋምቤላ የበላይነት ተጠናቋል፡፡ ሐረር በፎዚያ ሰኢድ የ8ኛ ደቂቃ ግብ ቀዳሚ መሆን ቢችሉም ኝቦኝ የም በ19 እና 65ኛው ደቂቃ ባስቆጠረቻቸው ግቦች ጋምቤላን ወደ መሪነት አሸጋግራለች፡፡ ዮዲት ልኡልሰገድ በ74ኛው ደቂቃ ሐረርን አቻ ስታደርግ አርያት ኡኮት በ76 እና 80ኛው ደቂቃ አከታትላ ባስቆጠረቻቸው ግቦች ጋምቤላን መሪ አድርጋለች፡፡ በመጨረሻም መደበኛው 80 ደቂቃ ተጠናቆ በጭማሪው ሁለተኛ ደቂቃ ኝቦኝ የም ሐት-ትሪክ የሰራችበትን ግብ ከመረብ አሳርፋ ደምቃ ውላለች፡፡ ጨዋታውም በጋምቤላ 5-2 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

PicsArt_1472237002184

በተመሳሳይ 09:30 ቢሾፍቱ ሜዳ ላይ ሊጀመር የታቀደለት የአፋር እና ኢትዮ ሶማሌ ጨዋታ የሶማሌ ቡድን መሪ ዘግይቶ በመድረሱ በ15 ደቂቃ ዘግይቶ ተጀምሯል፡፡

1-1 በሆነ አቻ ውጤት በተጠናቀቀው ጨዋታ ሀና ሰለሞን በ43ኛው ደቂቃ ኢትዮ ሶማሌን ቀዳሚ ስታደረግ ሀናን የሱፍ በ51ኛው ደቂቃ አፋርን በቅጣት ምት ግብ አቻ አድርጋለች፡፡

PicsArt_1472224716850

09:30 ለምለም ተስፋ ሜዳ ላይ አዲስ አበባ ድሬዳዋ ላይ ፍፁም የበላይነቱን አሳይቶ 5-0 አሸንፏል፡፡

ከአአ የድል ግቦች መሳይ ጉታ (በ54ኛ እና 62ኛ ደቂቃ) ሁለት ግቦች ስታስቆጥር ማህደር ወልዴ (18ኛ) ፣ ትዕግስት ሰለሞን (24ኛ) እና ቤተልሄም ሽመልስ (80+1ኛ) ቀሪዎቹን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

PicsArt_1472237056375

09:45 ቢሾፍቱ ሜዳ ላይ ኦሮሚያ ደቡብን 2-0 አሸንፏል፡፡ በጠዋታው ጥሩ ስትንቀሳቀስ የዋለችው ድርሻዬ መሃመድ በ4ኛው ደቂቃ ቀዳሚውን ስታስቆጥር ተቀይራ የገባችው መቅደስ ተስፋዬ በ75ኛው ደቂቃ ሁለተኛውን አክላለች፡፡

*ማስታወሻ

በዚህ ውድድር ተጋጣሚዎች የሚጫወቱት ሙሉ 90 ደቂቃ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሳይሆን 80 ደቂቃ ነው፡፡

የነገ ጨዋታዎች ፕሮግራም (ወንዶች)

ቅዳሜ ነሀሴ 21 ቀን 2008

05:00 ድሬዳዋ ከ ኦሮምያ (ቢሾፍቱ ሜዳ)

07:00 ሐረሪ ከ አማራ (ቢሾፍቱ ሜዳ)

09:00 አፋር ከ ጋምቤላ (ቢሾፍቱ ሜዳ)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *