በይድነቃቸው ተሰማ መታሰብያ ከ15 አመት በታች ውድድር ግማሽ ፍጻሜውን የተቀላቀሉ ቡድኖች ተለይተዋል

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ለ11ኛ ጊዜ ያዘጋጀው የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ መታሰቢያ ከ15 አመት በታች ውድድር ወደ መገባደጃው ምዕራፍ ደርሷል፡፡

ውድድሩ ከነሐሴ 1 ጀምሮ በ57 ቡድኖች መካከል መካኒሳ አካባቢ በሚገኘው ዶን ቦስኮ ሜዳ ሲካሄድ የሰነበተ ሲሆን ወደ ግማሽ ፍፃሜ ያለፉት ቡድኖች ተለይተዋል፡፡ በዚህ መሰረት የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ሐሙስ ነሀሴ 26 በአበበ ቢቂላ ስታድየም ሲካሄዱ 03:00 ላይ አፍሮ ፅዮን ከ መንግስቱ እና ልጆቹ ፤ 05:00 ጫካ ሜዳ ከ አሰላ ( የነገ ፍሬ) ይጫወታሉ፡፡

ውድድሩ በመጪው እሁድ አበበ ቢቂላ ስታድየም ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን 03:0 ላይ የደረጃ ፤ 04:00 ላይ የፍፃሜ ጨዋታ ይደረጋል፡፡

11ኛ አመቱን በያዘው የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ ውድድር አምና መንግስቱ እና ልጆቹ አፍሮ ፅዮን ኮንስትራክሽንን 1-0 በማሸነፍ ዋንጫ ማንሳቱ ይታወሳል፡፡

Leave a Reply