ኮፓ ኮካኮላ ፡ በ3ኛ ቀን ውሎ አማራ ፣ ደቡብ ፣ ኦሮምያ እና ቤኒሻንጉል ድል ቀንቷቸዋል

የኮፓ ኮካ ኮላ ከ15 አመት በታች የማጠቃለያ ውድድር በቢሾፍቱ መካሄዱን ቀጥሏል፡፡ 1 የወንዶች እና 4 የሴቶች ጨዋታዎችም ተደርገዋል፡፡

ለምለም ተስፋ ሜዳ 06፡00 ላይ የተደረገው የአዲስ አበባ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወንዶች ጨዋታ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ ሀብታሙ ገብረጊዮርጊስ በ49ኛው ደቂቃ አዲስ አበባን ቀዳመ ሲያደርግ አብዲ ህዝቅኤል ቤኒሻንጉልን አቻ ያደረገች ግብ በ69ኛው ደቂቃ በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል፡፡

07:00 ቢሾፍቱ ስታድየም ላይ በሴቶች ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ጋምቤላን 3-2 አሸንፏል፡፡ አቹል ኡማን በ11ኛው ደቂቃ ጋምቤላን ቀዳሚ ብታደርግም ሚልዮን ደረጄ ፣ ፅጌ አለማየሁ እና አሙና ኡመር በመጀመርያው አጋማሽ አከታትለው ባስቆጠሯቸው ግቦች ወደ መሪነት ተሸጋግረዋል፡፡ ሄዋን አየለ በ62ኛው ደቂቃ ግብ ብታስቆጥርም ጋምቤላን ከሽንፈት ማዳን አልቻለም፡፡

PicsArt_1472403465675

ለምለም ተስፋ ሜዳ 08:00 ላይ ደቡብ ከ ኢትዮጵያ ሶማሌ ያደረጉት ጨዋታ በደቡብ 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ትንሳኤ ሻንቆ በ9 እና 16ኛው ደቂቃ የደቡብን ግቦች ከመረብ አሳርፋለች፡፡

PicsArt_1472408013786

09:00 ላይ በቢሾፍቱ ስታድየም አማራ ድሬዳዋን 5-0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል፡፡ ከአማራ 5 ግቦች መካከል ትዕግስት አዲሱ 4ቱን በማስቆጠር ደምቃ ውላለች፡፡ ትዕግስት በ19ኛው ደቂቃ ከ25 ሜትር አካባቢ የመታችው ቅጣት ምት በተከላካዮች ሲመለስ በድጋሚ መትታ የመክፈቻውን ግብ ስታስቆጥር በ66ኛው እና 70ኛው ደቂቃ ከቅጣት ምት በቀጥታ መትታ ፣ በ76ኛው ደቂቃ ደግሞ በክፍት ጨዋታ አስቆጥራለች፡፡ ትዕግስት ያላት ጉልበት እና ከርቀት አክርራ የምትመታቸው ኳሶች የወደፊቱ የሴቶች እግርኳስ ኮከብ እንደምትሆን ፍንጭ የሰጠ ነበር፡፡ የአማራን ቀሪ ግብ ሰላም ካሱ አስቆጥራለች፡፡

PicsArt_1472403595637

በእለቱ የመጨረሻ ጨዋታ ለምለም ሜዳ ላይ በ10:00 ኦሮምያ አፋርን 2-0 አሸንፏል፡፡

ናርዶስ ሞጃ በ47ኛው ደቂቃ መክፈቻውን ስታስቆጥር እመቤት ደበላ በ52ኛው ደቂቃ ሁለተኛውን አክላለች፡፡

PicsArt_1472407958540


የሴቶች የደረጃ ሰንጠረዥ

ምድብ ሀ


ደረጃ.ክልል.ተጫ (ልዩነት) ነጥብ

1. ኦሮምያ 2 (+4) 6

2. ደቡብ 2 (0) 3

3. ኢትዮ ሶማሌ 2 (-2) 1

4. አፋር 2 (-2) 1


ምድብ ለ


ደረጃ.ክልል.ተጫ (ልዩነት) ነጥብ

1. ጋምቤላ 2 (+2) 3

2. ቤንሻንጉል 1 (+1) 3

3. ሐረሪ 1 (-3) 0


ምድብ ሐ

ደረጃ.ክልል.ተጫ (ልዩነት) ነጥብ

1. አዲስ አበባ 1 (+5) 3

2. አማራ 1 (+5) 3

3. ድሬዳዋ 2 (-10) 0


የነገ ፕሮግራሞች (የወንዶች)

*ሁሉም ጨዋታዎች ቢሾፍቱ ስታድየም ላይ ይደረጋሉ፡፡

03:00 ደቡብ ከ አፋር

05:00 ኢትዮ ሶማሌ ከ ሐረሪ

07:00 ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከ ድሬዳዋ

09:00 አዲስ አበባ ከ ኦሮምያ


Leave a Reply