ኮፓ ኮካኮላ ፡ በ4ኛ ቀን የማጠቀለያው ውሎ ኦሮምያ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፉን አረጋግጧል

የኮፓ ኮካ ኮላ ከ15 አመት በታች የማጠቃለያ ውድድር 4ኛ ቀኑን ይዟል፡፡ ዛሬበተደረጉት የወንዶች ጨዋታዎችም ኢትዮ ሶማሌ ፣ ደቡብ ፣ ኦሮምያ እና ቤኒሻንጉል አሸንፈዋል፡፡

ከምድብ ሐ ጠዋት 3፡00 ላይ ደቡብ ከ አፋር ያደረጉት ጨዋታ በደቡብ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ በ57ኛው ደቂቃ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ ተጠቅሞ የደቡብን ወሳኝ የድል ግብ ከመረብ ያሳረፈው እስጢፋኖስ ዘውዴ ነው፡፡ ጨዋታው ማለዳ ላይ በዘነበው ዝናብ ምክንያት ለሁለቱም ቡድኖች ፈታኝ የነበረ ሲሆን በተለይ አፋሮች በመጀመርያው ጨዋታ ያሳዩትን ግሩም እንቅስቃሴ እንዳይደግሙ አግዷቸዋል፡፡ በዚህ ምድብ ደቡብ ከ ጋምቤላ የሚያደርጉት ጨዋታ የምድቡን ሃላፊ የሚለይ ወሳኝ ጨዋታ ነው፡፡

PicsArt_1472492812897

የደረጃ ሰንጠረዥ

1 አፋር     2 (+3) 3

2 ደቡብ     1 (+1) 3

3 ጋምቤላ   1 (-4) 0


ከምድብ ለ 05፡00 ላይ ኢትዮ ሶማሌ ከ ሐረር ያደረጉት ጨዋታ በኢትዮ ሶማሌ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ኢትዮ ሶማሌ በመሃመድ አህመድ የ29ኛ ደቂቃ ግብ ቀዳሚ ሲሆን ካሌብ ጀማል በ31ኛው ደቂቃ የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ወደ ግብነት ቀይሮ ሐረርን አቻ አድርጓል፡፡ የኢትዮ ሶማሌን የማሸነፍያ ግብ በ2ኛው አጋማሽ ከመረብ ያሳረፈው መሃድ ሀሰን ነው፡፡ ሐረሪ ከምድቡ መውደቁን በማረጋፈጡ አማራ እና ኢትዮ ሶማሌ የሚያደርጉት የምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ሃላፊውን ይለያል፡፡

PicsArt_1472492723568

የደረጃ ሰንጠረዥ

1 ኢትዮ ሶማሌ    1 (+1) 3

2 አማራ           1 (0) 1

3 ሐረሪ           2 (-1) 1


በምድብ ሀ 07፡00 ላይ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ድሬዳዋን ገጥሞ 2-0 አሸንፏል፡፡ ቤንሻንጉል ትላንት በመጫወቱ በዛሬው ጨዋተው ተዳክሞ ይታያል ተብሎ ቢገመትም በተቃራኒው የእንቅስቃሴ የበላይነት አሳይተው ለማሸነፍ በቅተዋል፡፡

PicsArt_1472492643437

በዚሁ ምድብ 09፡00 ላይ ኦሮምያ አዲስ አበባ ከተማን 3-0 በመርታት ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፉን አረጋግጧል፡፡ በ25ኛው ደቂቃ ለሚ ረፍሶ ፣ በ33ኛው ደቂቃ ናትናኤል ብርሃኔ ፣ በ73ኛው ደቂቃ ዳንኤል አብርሃም የኦሮምያን የድል ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ ኦሮምያዎች እንደመጀመርያው ጨዋታ ሁሉ ዛሬም ምርጥ እንቅስቃሴ ያሳዩ ሲሆን ትላንት ጨዋታ ያደረጉት አዲስ አበባ ከተማዎች በአንፃሩ ተዳክመው ታይተዋል፡፡ ከዚህ ምድብ ኦሮምያ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፉን ፣ ድሬዳዋ ደግሞ መውደቁን በማረጋገጡ ኦሮምያ ከ ቤኒሻንጉል ፣ አዲስ አበባ ከድሬዳዋ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች በጥሩ ሁለተኛ ለማለፍ ለሚደረገው ፉክክር ወሳኝ ናቸው፡፡

የደረጃ ሰንጠረዥ

1 ኦሮምያ        2 (+4) 6

2 ቤኒሻንጉል    2 (+2) 4

3 አዲስ አበባ   2 (-3) 1

4 ድሬዳዋ      2 (-3) 0

የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዎች

ሴቶች – ማክሰኞ ነሀሴ 24

03:00 ኦሮምያ ከ ኢትዮ ሶማሌ (ለምለም ተስፋ ት/ቤት)
03:00 ደቡብ ከ አፋር (ቢሾፍቱ ስታድየም)
05:00 ሀረሪ ከ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ (ለምለም ተስፋ ት/ቤት)
05:00 አዲስ አበባ ከ አማራ (ቢሾፍቱ ስታድየም)

የወንዶች – ረቡዕ ነሀሴ 25

03:00 አዲስ አበባ ከ ድሬዳዋ (ቢሾፍቱ ስታድየም)
03:00 ኦሮምያ ከ ቤኒሻንጉል (ለምለም ተስፋ ት/ቤት)
05:00 አማራ ከ ኢትዮ ሶማሌ (ለምለም ተስፋ ት/ቤት)
05:00 ጋምቤላ ከ ደቡብ (ቢሾፍቱ ስታድየም)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *