ኮፓ ኮካ ኮላ፡ የወንዶች የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ተጠናቀዋል

የኮፓ ኮካኮላ ከ15 አመት በታች የማጠቃለያ ውድድር በቢሾፍቱ ከተጀመረ 6ኛ ቀኑን ይዟል፡፡ በዛሬው እለትም የወንዶች የምድብ ጨዋታዎች ተጠናቀዋል፡፡

በምድብ ሀ 03:00 ላይ በለምለም ተስፋ ት/ቤት ኦሮምያ ቤኒሻንጉልን 1-0 በማሸነፍ በሙሉ 9 ነጥብ የምድቡ የበላይ ሆኗል፡፡ ዳንኤል አብርሃም የኦሮምያን ግብ በ31ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ኦሮምያዎች በሁለቱም ጾታ ሙሉ 9 ነጥብ ይዘው ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማለፍ ችለዋል፡፡

ፎቶ - ታላቁ
ፎቶ – ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ

ከዚሁ ምድብ በተመሳሳይ ሰአት ቢሾፍቱ ላይ አዲስ አበባ በ ድሬዳዋ 3-1 ተሸንፎ የማለፍ እድሉን ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡ አዲስ አበባዎች ብሩክ ማህተሜ በ6ኛው ደቂቃ 3 ተጫዋቾችን አልፎ ባስቆጠራት ግሩም ግብ ቀዳሚ መሆን ቢችሉም ድሬዎች በ34ኛው እና 64ኛው ደቂቃ በአቤል ታደሰ ፣ በ42ኛው ደቂቃ ዮናስ በላይ ባስቆጠሯቸው ግቦች አሸንፈው ወጥተዋል፡፡

ከዚህ ምድብ ኦሮምያ እና ቤኒሻንጉል ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ፎ
ፎቶ – ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ

የደረጃ ሰንጠረዥ

1 ኦሮምያ         3 (+5) 9

2 ቤኒሻንጉል    3 (+1) 4

– – – – – – –

3 ድሬዳዋ        3 (-1) 3

4 አዲስ አበባ  3 (-5) 1

በምድብ ለ 05:00 ላይ ከምድቡ ለማለፍ አማራ ከ ኢትዮ ሶማሌ ያደረጉት ወሳኝ ጨዋታ በአማራ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ሀብታሙ አረጋ በ15ኛው ደቂቃ አማራን ቀዳሚ ሲያደርግ መሃድ ሀሰን ኢትዮ ሶማሌን በ32ኛው ደቂቃ አቻ አድርጓል፡፡ የአማራን ወሳኝ የድል ግብ ከመረብ ያሳረፈው ሞላዬ አከለ በ53ኛው ደቂቃ ነው፡፡

PicsArt_1472648068614
ፎቶ – ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ

የደረጃ ሰንጠረዥ

1 አማራ             2 (+1) 4

– – – – – – –

2 ኢትዮ ሶማሌ   2 (+0) 3

3 ሐረሪ              2 (-1) 1

በምድብ ሐ 05:00 ላይ ደቡብ ጋምቤላን 3-0 በመርታት ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል፡፡ እስጢፋኖስ ዘውዴ በ33 ኦና 43ኛው ደቂቃ ሁለት ግቦች ሲያስቆጥር አቤኔዘር ህዝቅኤል በ31ኛው ደቂቃ ቀሪዋን ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡ የእስጢፋኖስ ሁለተኛ ግብ በውድድሩ ከታዩት ግሩሞ ግቦች መካከል የምትጠቀስ ነበረች፡፡

PicsArt_1472647367221

የደረጃ ሰንጠረዥ

1 ደቡብ     2 (+4) 6

– – – – – –

2 አፋር     2 (+3) 3

3 ጋምቤላ   2 (-7) 0

የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች

(ሁሉም ጨዋታዎች በቢሾፍቱ ስታድየም ይደረጋሉ፡፡)

* ሴቶች (ሀሙስ ነሀሴ 26 ቀን 2008)

03:00 ኦሮምያ ከ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ

05:00 አዲስ አበባ ከ ደቡብ

*ወንዶች (አርብ ነሀሴ 27 ቀን 2008)

03:00 ኦሮምያ ከ አማራ

05:00 ደቡብ ከ ቤኒሻንጉል

Leave a Reply