የኢትዮጵያ U17 ብሄራዊ ቡድን ዝግጅት ሲጀምር አዳዲስ ተጫዋቾችንም አካቷል

የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ከ17 አመት በታች ዋንጫ ማጣርያ ከማሊ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ዝግጅቱን ዛሬ ጀምሯል፡፡

በአዲስ አበባ ስታድየም የመሮጫ መም ላይ በነበረው ልምምድ ለተጫዋቾቹ የፍጥነትና የአካል ብቃት ሙከራ ተደርጎላቸዋል፡፡

PicsArt_1472670679745

አሰልጣኝ አጥናፉ አባተ በሀዋሳ እየተካሄደ ከሚገኘው የክልል ፕሮጀክቶች የምዘና ውድድር እና ወላይታ ድቻ ተጫዋቾችን በመመልመል የተመለሱ ሲሆን ተጫዋቾቹ የMRI ምርመራ አድርገው ተገቢ ከሆኑ ከቡድኑ ጋር ይቀላቀላሉ ተብሏል፡፡

በረከት መንገሻው ፣ አስቻለው ግርማ እና ፉአድ ተማም ከወላይታ ድቻ የተመረጡ ሲሆን ፉአድ ዘንድሮ በካፋ ቡና ድንቅ አቋሙን አሳይቶ ወደ ድቻ የተዘዋወረ ተጫዋች ነው፡፡

ፍቃደ ስላሴ ደሳለኝ ፣ ፍፁም ተስፋዬ ፣ በረከት ግርማ ፣ ማቲዮስ መርኪን እና ይፍታለም ታፈሰ ደግሞ ከፕሮጀክቶቹ የምዘና ውድድር የተመረጡ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

1 Comment

  1. B Hawasa iyatakahed balewu ye keleloch wudeder ye club malemayoch pls y oromiyan techawachoch lay tikuret yidareg
    wow players oromiya
    1Duresa
    2Ashanafe
    3Abdi

Leave a Reply