ኮፓ ኮካኮላ ፡ ኦሮምያ እና ደቡብ በሴቶች ለፍጻሜ አልፈዋል

የኮፓ ኮካኮላ ከ15 አመት በታች የማጠቃለያ ውድድር የሴቶች የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ተካሂደው ኦሮምያ እና ደቡብ ለፍጻሜው አልፈዋል፡፡

03:00 ቢሾፍቱ ስታድየም ላይ ኦሮምያ ቤኒሻንጉል ጉሙዝን 2-0 በመርታት ወደ ፍጻሜው አልፏል፡፡

የመጀመርያው አጋማሽ ካለግብ የተጠናቀቀ ሲሆን ተመጣጣኝ ፉክክርም ተስተናግዶበታል፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ ተጠናክረው የቀረቡት ኦሮምያዎች እድላዊት ቢንያም በ47ኛው እና ድርሻዬ መሃመድ በ75ኛው ደቂቃ ግቦች አስቆጥረው 2-0 በማሸነፍ ወደ ፍጻሜው አልፏል፡፡

PicsArt_1472731078693

05:00 ላይ ደቡብ አዲስ አበባን 3-0 በማሸነፍ በፍጻሜው ኦሮምያን ተቀላቅሏል፡፡ ጤናዬ ለታሞ የመጀመርያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ 1 ደቂቃ ሲቀረው ቀዳሚውን ግብ ስታስቆጥር ጤናዬ በድጋሚ በ60ኛው እንዲሁም ብዙአየሁ ፀደቀ በራሷ ግብ ላይ በ77ኛው ደቂቃ የደቡብን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

ደቡብ እና ኦሮምያ ለዋንጫ እሁድ 02:00 ላይ ሲጫወቱ ቤኒሻንጉል ከ ከዲስ አበባ ለደረጃ ቅዳሜ 09:00 ይጫወታሉ፡፡

የነገ ፕሮግራም

*ወንዶች

03:00 ኦሮምያ ከ አማራ

05:00 ደቡብ ከ ቤኒሻንጉል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *