​አቤል ማሞ በቅርቡ ወደ ሜዳ ይመለሳል

ብሄራዊ ቡድኑ በሀዋሳ ዝግጅት በሚያደርግበት ወቅት ጉዳት ያጋጠመው ግብ ጠባቂው አቤል ማሞ ከጉዳቱ እያገገመ ይገኛል፡፡

ሙገር ሲሚንቶን ለቆ መከላከያን የተቀላቀለው አቤል ያጋጠመው ጉዳት ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ያርቀዋል ቢባልም ሙሉ ለሙሉ ከጉዳቱ በማገገም ላይ እንደሆነና በቅርብ ቀናት ውስጥ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ ለሶከር ኢትዮዽያ ተናግሯል፡፡

” ጉዳቱ መጀመርያ ላየው ሰው ፣ ለኔም ከባድ መስሎኝ ነበር፡፡ ሆኖም በህክምና ባለሙያዎች ጥረት አሁን ከጉዳቴ በጥሩ ሁኔታ እያገገምኩ ነው፡፡ በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ሜዳ እመለሳለው” ብሏል፡፡

አቤል በተጠናቀቀው አመት የብሄራዊ ቡድኑ ዋና ግብ ጠባቂ የነበረ ሲሆን በኢትዮዽያ አስተናጋጅነት በተካሄደው ሴካፋ ላይ ሁለት ጊዜ የጨዋታው ኮከብ ተሸላሚ መሆኑ ይታወሳል፡፡

 

Leave a Reply