ሳላዲን ሰዒድ እና ዋሊድ አታ ስለሲሸልሱ ጨዋታ ይናገራሉ

ጋቦን ለምታስተናግደው የ2017 ቶታል አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚደረጉት የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች በዚህ ሳምንት ይጠናቀቃሉ፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንም ከሲሸልስ ጋር በሃዋሳ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ቅዳሜ 10፡00 ይጫወታል፡፡

አጥቂው ሳላዲን ሰዒድ እና ተከላካዩ ዋሊድ አታ በብሄራዊ ቡድኑ ወደ አፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ተስፋ እና ዝግጅት ዙሪያ ለሶከር ኢትዮጵያ የሰጡትን አስተያየት እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል፡፡

“ለማሸነፍ ነው የምንገባው” ሳላዲን ሰዒድ

ስለዝግጅት

“ያው ጥሩ ዝግጅት አድርገናል፡፡ አንድ ወር እዚህ (ሃዋሳ) ነበርን፡፡ ሁሉም ተጫዋች በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል፡፡ ሁሉም ነገር ጥሩ ነው፡፡”

የማለፍ ተስፋ

“በእግርኳስ የሚከሰተው ነገር አይታወቅም፡፡ ዋናው እኛ ለማሸነፍ ነው የምንገባው፡፡ ማለፍ አለማለፋችን ከዛ በኃላ ነው የሚታወቀው፡፡”

PicsArt_1472823088237

“ሶስት ነጥብ እንደምናሳካ ተስፋ አለኝ” ዋሊድ አታ

ስለዝግጅት

“ዝግጅት ጥሩ ነው፡፡ በጥሩ መልኩ ልምምዳችን ስንሰራ ነበር፡፡ ነገ የጨዋታው ግዜ ነው ፤ ስለዚህ ዝግጁ ነን፡፡”

ስለማለፍ ተስፋ

“የቡድን መንፈሱ እንደምታየው ነው፡፡ ጥሩ እና ደስ የሚል የቡድን መንፈስ አለን፡፡ ከአሁኑ ለቅዳሜው ጨዋታ ጓጉቻለው፡፡ ሙሉ ሶስት ነጥብ እንደምናሳካ ተስፋ አለኝ፡፡ በሌሎች ምድቦች ጨዋታ እኛ እንደምፈልገው መልኩ ከሄደ በአፍሪካው ዋንጫ እንጫወታለን፡፡”

ስለሃዋሳ ቆይታው

“ጥሩ ነው፡፡ ከዚህ በፊት አዲስ አበባ ብቻ ነው ተጫውቼ የማውቀው፡፡ አሁን ደግሞ ወደ ሃዋሳ መጥቻለው፡፡ እውነት ለመናገር ሃዋሳ ቆንጆ ነው፡፡ ስታዲየሙም አዲስ ነው፡፡ ሁሉም ነገር መልካም ነው፡፡”

ከገልሰንበርሊጊ ወደ ኦስተርሰንድስ በውድድር ዘመኑ አጋማሽ ስላደረገው ዝውውር

“ወደ ቤቴ ተመልሻለው ለዚህም ደስተኛ ነኝ፡፡ በቱርክ ቆይታዬ እንድምታውቀው ብዙም አልተጫወኩም፡፡ አሁን ወደ ስዊድን ተመልሻለው፡፡ ከዚህ በፊት የተጫወትኩበት ሊግ ስለሆነ ብዙም አልቸገረኝም፡፡ በዚህም ደስተኛ ነኝ፡፡”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *