የሲሸልስ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ የመጀመርያ ልምምዱን በሀዋሳ ሰርቷል፡፡ ትላንት ማምሻውን አአ ገብቶ ዛሬ ሀዋሳ የመጣው የሲሸልስ ብሄራዊ ቡድን 11:00 ላይ ቀለል ያሉ እና የቆሙ ኳሶች ልምምድ በሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስቴዲዮም ሰርቷል፡፡
የሲሸልስ ብሄራዊ ቡድን 21 የልኢ።ካን ቡድን አባላት ይዞ ኢትዮጵያ የመጣ ሲሆን ከነዚህ መካከል 19ኙተጫዋቾች ናቸው፡፡ ተጨማሪ አምስት አባላት ደግሞ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ የሚገቡ ይሆናል፡፡
የኢትዮዽያ ብሄራዊ ቡድን በበኩሉ ዛሬ ረፋድ ላይ የመጨረሻ ልምምዱን አከናውኗል፡፡ በዛሬው ልምምድ የቆሙ ኳሶችን የመምታት ልምምድ የሰሩ ሲሆን አሰልጣኝ ገብረመድህን ለነገው ጨዋታ የሚጠቀሙባቸውን 18 ተጫዋቾች ዛሬ ያሳውቃሉ፡፡ አቤል ማሞ ፣ እንዳለ ከበደ እና አህመድ ረሺድ በጉዳት ከ18ቱ ውጪ መሆናቸው የተረጋገጡ ተጫዋቾች ናቸው፡፡
ጨዋታውን የሚመሩት ዳኞች