ለሲሸልሱ ጨዋታ የዋልያዎቹ የመጀመርያ ተሰላፊዎች ታውቀዋል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 10:00 ላይ ከሲሸልስ ለሚያደርገው ጨዋታ ስብስቡን ወደ 18 ዝቅ አድርጓል፡፡

አሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይሌ የመስመር ተከላካዩን ስዩም ተስፋዬ የዋሊያዎቹ አምበል ያደረጉ ሲሆን ስዩም ቡድኑን እየመራ ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡

ከ24 ወደ 18 ስብስቡን የቀነሰው ብሄራዊ ቡድኑ ግብ ጠባቂው ሳምሶን አሰፋን፣ ተከላካዩ አዲስ ተስፋዬ፣ የመስመር ተጫዋቾቹ ታደለ መንገሻ እና አዲስ ግደይ እንዲሁም የፊት አጥቂው ታፈሰ ተስፋዬ ከ18ቱ ውጪ የሆኑ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

የብሄራዊ ቡድኑ ቋሚ አሰላለፍም ከሞላ ጎደል ታውቋል፡፡

ጀማል ጣሰው

ስዩም ተስፋዬ (አምበል) ፣ ሙጂብ ቃሲም ፣ አንተነህ ተስፋዬ ፣ አብዱልከሪም መሃመድ

ሽመክት ጉግሳ፣ ጋቶች ፓኖም፣ ሽመልስ በቀለ፣ ኤፍሬም አሻሞ

ሳላዲን ሰዒድ፣ ጌታነህ ከበደ

 

ተጠባባቂዎች

ተክለማሪያም ሻንቆ

ቴዎድስ በቀለ

መሃሪ መና

ኤልያስ ማሞ

አስራት መገርሳ

በሃይሉ አሰፋ

ዳዊት ፍቃዱ

 

ማስታወሻ፡ ዋሊድ አታ ህመም ያጋጠመው ሲሆን የህክምና ቡድኑ ለጨዋታው ብቁ ይሁን አይሁን የወሰነው ውሳኔ የለም፡፡ ዋሊድ ለጨዋታው ብቁ ካልሆነ ቴዎድሮስ በቀለ ይተካዋል፡፡ ከ18ቱ ውጪ የነበረው አንተነህ ተስፋዬ ደግሞ ተጠባባቂ ይሆናል፡፡ ዋሊድ ወደ ሜዳ የሚገባ ከሆነ ግን ቴዎድሮስ ተጠባባቂ ሆኖ አንተነህ ከቡድኑ ውጪ ይሆናል፡፡

ሴንትራል ሀዋሳ ሆቴል ይህንን ዘገባ ወደ እናንተ እንዲደርስ እገዛ ስላደረገልን እናመሰግናለን።

4 Comments

  1. Where is king tafese tesfaye….1000 etef aun balachew akuam le sala yeshalal

Leave a Reply