​” የተጋጣሚያችን የመከላከል አጨዋወት በርካታ ግቦች እንዳናስቆጥር አግዶናል ” ገብረመድህን ኃይሌ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ2017ቱ የጋቦን የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታውን ዛሬ ሃዋሳ ኢንተርናሽናል ስታድየም ከሲሸልስ ጋር አድርጎ በድል አጠናቋል።
የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ የሆኑት አሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይሌ ከጨዋታው በኃላ አስተያየታቸውን ሰተዋል።

ስለ ጨዋታው

“ዛሬ ካሰብነው ነገር አንጻር 100% እቅዳችንን አሳክተናል ማለት ባይቻልም ማሸነፍ ስለሆነ ዋነኛ ግባችን በማሸነፋችን ደስተኞች ነኝ፡፡ ነገር ግን የምንፈልገውን ያክል ግቦችን ባለማስቆጠራችን ቅር ብሎናል።”

“ተጋጣሚያችን በጣም ተከላክሎ ሲጫወት ነበር ይህ ደግሞ እንዳሰብነው አጥቅተን ብዙ ጎሎችን እንዳናስቆጥር አድርጎናል። በተለይ ደግሞ እነሱ ረጃጅም ተጨዋቾች አላቸው፡፡ ግብ ያስቆጠረብንን ተጨዋች ጨምሮ ለዛም ነው ጎሎችን ያላስቆጠርነው።”

ጥሩ እና ደካማ ጎን

“በዛሬው ጨዋታ ላይ ሁላችሁም እንዳያችሁት ሁለት ሶስት የሚሆኑ ለጎል የቀረቡ ኳሶችን አባክነናል፡፡ ይህ ደግሞ በዋናነት እንደ ክፍተት የምናየው ድክመታችን ነበር።”

“ከጨዋታው ብዙ ነገሮችን ተምረናል አንድ ቡድን ጨዋታን በትግስት ማጠናቀቅ እንዳለበት እና ያዋጣኛል ብሎ የሚያስበውን የጨዋታ ዘይቤ እስከመጨረሻው መቀጠል እንዳለበት ለወደፊቱ ትምህርት ወስደናል።”

“ተጨዋቾቼ ከ70-80% በላይ በታክቲኩ ረገድ ጥሩ ነበሩ። ሁሉም በቦታቸው ጥሩ ሲጫወቱ ነበር ከዚህም በላይ ባሉን ተጨዋቾች የበለጠ መስራት እንደምንችል ያሳየ ጨዋታ ነው።”

ስለ ጌታነህ ከበደ

“ጌታነህ ጥሩ ተጨዋቾች ነው፡  እስካሁን ለቡድኑ ብዙ ግቦችን አስቆጥሮ ነጥቦችን እንድንይዝ አድርጎናል። ሁላችሁም እንዳያችሁት ዛሬም ግብ እስቆጥሮዋል ወደፊትም ግብ ማስቆጠሩን ይቀጥላል፡፡”

 

CH

ሴንትራል ሀዋሳ ሆቴል ይህንን ዘገባ ወደ እናንተ እንዲደርስ እገዛ ስላደረገ እናመሰግናለን።

Leave a Reply