ኪንግስሌይ ንዋንኮ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ…

ናይጄሪያዊው አጥቂ ኪንግስሌይ ንዋንኮ ለቅዱስ ጊዮርጊስ እንደፈረመ እየተነገረ ይገኛል

የ2006 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮኮብ ግብ አግቢ የነበረው ኡመድ ኡክሪ መልቀቅ በአጥቂ መስመራቸው ላይ የፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት የተለያዩ ተጫዋቾችን እየሞከሩ የሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በቱርክ 2ተኛ ዲቪዝዮን በተለያዩ ክለቦች የመጫወት ልምድ ያለውን ናይጄሪያዊ አጥቂ ኪንግስሌይ ንዋንኮ ማስፈረማቸው ተሰምቷል። ንዋንኮ በ2013 ከዴንዚሊስፖር ከለቀቀ በኋላ ክለብ ማግኘት ያልቻለ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስን የሚቀላቀል ከሆነ በነፃ ዝውውር ይሆናል።

ከንዋንኮ በተጨማሪ የኡጋንዳ ብሔራዊ ቡድን እና ኬሲሲኤ ክለብ ግብ አዳኝ የሆነው ብራያን ኡሞኒ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከፈረሰኞቹ ጋር ልምምድ እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል። በቅርቡ የግብፁ ክለብ ኢቲሃድ አሌክሳንድሪያ የ4 ወር ደሞዙን መክፈል ባለመቻሉ ወደ አዲስ አበባ የተመለሰው ኢመድ ኡክሪም ከፊፋ ከኮንትራቱ ነፃ እንደሆነ የሚገልፅ ደብዳቤ (Clearance) ካገኘ እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ ለመጫወት የቀድሞ ክለቡን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም በታህሳስ ወር አጋማሽ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ የሶስት ቀናት የሙከራ ጊዜ በማሳለፍ ጥሩ እንቅስቃሴ ያደረገው ኬንያዊ አጥቂ ጄሲ ዌሬ በቅዱስ ጊዮርጊስ እንደማይፈለግ ታውቋል።

Player Profile
Name: Kingsley Taiwo Nwanko
Date of Birth: September 20, 1988
Age: 26
Place of Birth: Lagos, Nigeria
Height: 1.77 m
Position: Center Forward
Favourite Foot: Right
Previous Clubs: Enugu Rangers (Nigeria – NPFL) – 2011
Tavsanil Linyitspor (TFF First League – Turkey) 2011-2012
Boluspor (TFF First League – Turkey) 2012
Denzilispor (TFF First League – Turkey) 2013

 

ያጋሩ