የ2008 የኮፓ ኮካኮላ ከ15 አመት በታች የማጠቃለያ ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡ በወንዶች ደቡብ ፣ በሴቶች ኦሮሚያ የዋንጫ ባለቤት ሆነዋል፡፡
02:30 ላይ በኦሮሚያ ከ ደቡብ በተደረገው የሴቶች የፍጻሜ ጨዋታ ኦሮሚያ በመለያ ምቶች አሸንፏል፡፡ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ የተጠናቀቀ ሲሆን በመለያ ምቶች ኦሮሚያ 3-1 አሸንፏል፡፡
ትላንት በተደረገው የደረጃ ጨዋታ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ አዲስ አበባን 4-0 በማሸነፍ 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡
በወንዶች የፍጻሜ ጨዋታ ደቡብ አማራን በመለያ ምቶች አሸንፏል፡፡ እንደ ሴቶች ሁሉ ይህም ጨዋታ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ካለግብ የተጠናቀቀ ሲሆን በመለያ ምቶች ደቡብ 4-2 አሸንፏል፡፡
ማለዳ ላይ በለምለም ት/ቤት ሜዳ በተደረገው የደረጃ ጨዋታ ቤኒሻንጉል ኦሮምያን 3-2 በማሸነፍ 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡
የፍጻሜ ጨዋታዎችን ተከትሎ ያማረ የመዝጊያ ስነስርአት ፣ ንግግሮች እና የሽልማት ስነስርአቶች የቀጠሉ ሲሆን ለኮከቦችም ሸልማት ተሰጥቷል፡፡
በወንዶች
ኮከብ ተጫዋች – አቤኔዘር ህዝቅኤል (ደቡብ)
ኮከብ ግብ አስቆጣሪ – እስጢፋኖስ ዘውዴ (5 ጎል – ደቡብ)
ኮከብ ግብ ጠባቂ – ዳንኤል ሰይፉ (ደቡብ)
ኮከብ አሰልጣኝ – ይብራ መሃሪ (ደቡብ)
የስፖርታዊ ጨዋነት ዋንጫ – ደቡብ
ተገቢ እድሜ – በተገቢ እድሜ በማሰለፍ – ደቡብ 1ኛ ፣ ኦሮሚያ 2ኛ ደረጃ አግኝተው የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል
ዳኞች
ዋና ዳኛ – አብዲ ከድር
1ኛ ረዳት ዳኛ – ኤፍሬም ኃይሉ
2ኛ ረዳት ዳኛ – አወቀ ጌታቸው
4ኛ ዳኛ – ስለሺ ገብሬ
ኮሚሽነር – አርአያ ደቻሳ
1ኛ. ደቡብ – 50,000 ፣ ዋንጫ እና የወርቅ ሜዳልያ
2ኛ. አማራ – 30,00 እና የብር ሜዳልያ
3ኛ. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ – 20,000 እና የነሀስ ሜዳልያ
በሴቶች
ኮከብ ተጫዋች – ፌቨን ተስፋዬ (ኦሮሚያ)
ኮከብ ግብ አስቆጣሪ – ትዕግስት አዲሱ (አማራ – 5ጎል)
ኮከብ አሰልጣኝ – ኤልሳቤጥ ምንዳዬ (ኦሮሚያ)
ኮከብ ግብ ጠባቂ – ዮርዳኖስ ኃይሌ (ኦሮሚያ)
የስፖርታዊ ጨዋነት ዋንጫ – ኦሮሚያ
በተገቢ እድሜ በማሰለፍ – ኢትዮ ሶማሌ 1ኛ ፣ አዲስ አበባ 2ኛ ደረጃ አግኝተው የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል
ዳኞች
ዋና ዳኛ – ገነት ታደሰ
1ኛ ረዳት ዳኛ – አዜብ አየለ
2ኛ ረዳት ዳኛ – አየለች አደሬ
4ኛ ዳኛ – አስናቀች ገብሩ
ኮሚሽነር – ተስፋነሽ ወረታ
1ኛ. ኦሮሚያ – 50,000 ፣ ዋንጫ እና የወርቅ ሜዳልያ
2ኛ. ደቡብ – 30,000 እና የብር ሜዳልያ
3. ቤኒሻንጉል – 20,00 ብር እና የነሀስ ሜዳልያ
በመላ ሃገሪቱ የሚገኙ 1,500 ት/ቤቶች እና 27 ሺህ ተማሪዎችን ያሳተፈው የኮፓ ኮካኮላ የ2008 የውድድር ዘመን የማጠቃለያ ውድድሩን በቢሾፍቱ አስተናጋጅነት ከነሀሴ 20 እስከ ነሀሴ 29 አከናውኖ በድምቀት ተጠናቋል፡፡
በውድድሩ በርከታ ባለ ተሰጥኦ ታዳጊዎች ከመታየታቸው በተጨማሪ የውድድር እና የፉክክር መንፈስ በታዳጊዎች ላይ እንዲሰርፅ ያደረገ ሆኖ አልፏል፡፡