​የአስራት መገርሳ ማረፊያ ደደቢት ሆኗል

ደደቢት የዳሽን ቢራው አማካይ አስራት መገርሳን የግሉ አድርጓል፡፡
በክረምቱ ከበርካታ ክለቦች ጋር ስሙ ተያይዞ ሲነሳ የከረመው አስራት ከዳሽን ቢራ ጋር የነበረውን ቀሪ የ1 አመት ኮንትራት በስምምነት አፍርሶ ለደደቢት ፈርሟል፡፡

ደደቢት አስራት መገርሳን የሁለት አመት ኮንትራት ያሰፈረመው ሲሆን የክንትራቱ ዋጋ አልተገለፀም፡፡

አስራት ከሰለሞን ሐብቴ እና ኤፍሬም አሻሞ በመቀጠል የደደቢት የክረምቱ 3ኛ ፈራሚ ሆኗል፡፡
በ2005 ክረምት ኤሌክትሪክን ለቆ በወቅቱ ከፍተኛ ሂሳብ ዳሽን ቢራን የተቀላቀለው አስራት ከ3 የውድድር ዘመናት ቆይታ በኋላ ከፕሪሚየር ሊጉ የወረደው ዳሽንን ለቆ ለደደቢት መፈረሙ ከሳሙኤል ሳኑሚ ፣ ተካልኝ ደጀኔ ፣ ኄኖክ ኢሳያስ እና ያሬድ ዝናቡ ጋር ለተለያየው ክለብ ጥንካሬን የሚሰጥ ነው፡፡[socialpoll id=”2385802″]

[socialpoll id=”2385807″]

1 Comment

Leave a Reply