የሰኞ ነሀሴ 30 ምሽት አጫጭር የዝውውር ዜናዎች

ሳላዲን በቅዱስ ጊዮርጊስ ለመቆየት አስቧል

ሞሊዲያ ክለብ ደ አልጀርን ለቆ በውድድር ዘመኑ አጋማሽ ቅዱስ ጊዮርጊስን የተቀላቀለው ሳላዲን ሰኢድ ለከርሞ በፈረሰኞቹ ቤት ለመቆየት ማሰቡን ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግሯል፡፡

“በቀጣይ የ2009 የውድድር ዘመን በቅዱስ ጊዮርጊስ ለመቆየት አስቤያለው” ብሏል፡፡

በተያያዘ ቅዱስ ጊዮርጊስ 4 ተጫዋቾችን ከቡርኪናፋሶ እና ካሜሩን አስመጥቶ የሙከራ ጊዜ እያሳለፉ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ፋሲል ከተማ 3 ተጫዋቾች አስፈርሟል

የ2008 የከፍተኛ ሊጉ አሸናፊ ፋሲል ከተማ በቀጣይ አመት እራሱን ለማጠናከር ተጨዋቾችን ማስፈረሙን ቀጥሏል።

ፋሲል አምሳሉ ጥላሁን እና ኤርሚያስ ኃይሉን ከዳሽን ቢራ ሲያስፈርም ድሬዳዋ ከተማ እንደፈረመ ሲነገርለት የነበረው የመድኑ ግብ አዳኝ ሀብታሙ ወልዴ በፌደሬሽኑ በይፋ ባለመረጋገጡ ወደ ፋሲል አምርቷል፡፡

ፋሲል የሶስቱ ተጫዋቾች ፊርማን ከማግኘቱ በተጨማሪ ያሬድ ባየህን ለማስፈረም የተቃረበ ሲሆን አሰልጣኝ ዘማርያም የአጥቂ እና የአማካይ ስፍራ ተጫዋቾችን ለማስፈረም እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ሀዋሳ 6 ተጫዋቾችን ወደ ዋናው ቡድን አሳድጓል

የሃዋሳ ከተማው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለስልጠና ወደ ጀርመን ማምራታቸውን ተከትሎ በአዲሱ ረዳት አሰልጣን ሙሉጌታ ምህረት አማካኝነት ዝግጅታቸውን በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

ሙሉጌታ ምህረት ስድስት የሀ-17 ተጨዋቾችን ወደ ዋናው ቡድኑ እንዳሳደገ የታወቀ ሲሆን አምና በጋቦኑ ሲኤፍ ሞናና ውድድር አመቱን ያሳለፈው ቶጓዊው ግብ ጠባቂ ሜንሳ ሶሆሆን አስመጥተዋል።


ድሬዳዋ ከተማ በረከት ሳሙኤልን አስፈርሟል

በርካታ ተጨዋችችን በማስፈረም ላይ የሚገኙት የድሬዳዋ ከተማው አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው የተከላካይ ክፍላቸውን ለማጠናከር የሙገር ሲሚንቶው አምበል በረከት ሳሙኤልን አስፈርመዋል።


አርባምንጭ የእንዳለ ከበደን ውል አድሷል

የቡድኑን ቁልፍ ተጨዋቾች ለማቆየት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው አርባምንጭ ከተማ እንዳለ ከበደን ለሁለት አመት በማስፈረም እፎይታ ቢያገኝም የታደለ መንገሻን ፊርማ እሰስካሁን ማረጋገጥ አልቻሉም፡፡


ወልድያ በዝውውር ገበያው ተቸግሯል

በ2007 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ተሰናብቶ ወደ ታችኛው የሊግ እርከን በወረደ በአመቱ ወደ ዋናው ሊግ ያደገው ወልድያ ቡድኑን ለማጠናከር መቸገሩ ታውቋል፡፡ አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ አይናቸው ያረፈባቸውን ተጫዋቾች ወደ ክለባቸው ለማምጣት ቢጥሩም አብዛኞቹ ለሌላ ክለብ በመፈረማቸው ስራቸውን ፈታኝ አድርጎባቸዋል፡፡

አንጋፋው አጥቂ አንዱአለም ንጉሴ በክረምቱ ለወልድያ የፈረመ ብቸኛ ተጫዋች ነው፡፡[socialpoll id=”2385802″]

[socialpoll id=”2385807″]

ያጋሩ

Leave a Reply