ኬንያ የ2016 ሴካፋ የሃገራት እና የክለብ ውድድሮችን ታስተናግዳለች

ኬንያ የዘንድሮውን የሴካፋ ዋንጫ እና የካጋሜ ክለብ ዋንጫን እንደምታስተናግድ ታውቋል፡፡

የሴካፋ ዋና ጸሃፊ ኒክላስ ሙሱንዬ ይፋ እንዳደረጉት ኬንያ የዘንድሮውን የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ በህዳር ወር ታስተናግዳለች፡፡

በሰኔ ወር ታንዛንያ ዳሬሰላም ላይ ሊደረግ የነበረው የሴካፋ ክለቦች ዋንጫ ታንዛንያ እንደማታስተናገግድ ይፋ ካደረገች በኋላ ሌላ አዘጋጅ ሃገር ሳይገኝ የቆየ ሲሆን ኬንያ በመጪው ታህሳስ ወር ላይ ውድድሩን ለማስተናገድ ፍቃደኝነቷን አሳይታለች፡፡

picsart_1473335592607

በሌላ በኩል ሴካፋ ለሁለተኛ ጊዜ ለማካሄድ ያቀደው የናይል ቤዚን ውድድር መሰረዙ ታውቋል፡፡

ኬንያ የሴካፋ ሀገራት ዋንጫን ከ2013 በኋላ ፣ የክለቦች ዋንጫን ከ2001 ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ታስተናግዳለች፡፡ የአምናው የሴካፋ ውድድር በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት መካሄዱ የሚታወስ ነው፡፡

ሴካፋ የሴቶች ዋንጫን ለመጀመርያ ጊዜ ከመስከረም 1 ጀምሮ በዩጋንዳ ሲያካሂድ የወንዶች በህዳር ወር ፣ የክለቦች በታህሳስ ወር እንዲሁም ከ17 አመት በታች ወንዶች ውድድር ደግሞ በግንቦት ወር ያካሂዳል፡፡


[socialpoll id=”2385802″]

[socialpoll id=”2385807″]

Leave a Reply