የሉሲዎቹ ተጫዋቾች ስለ ሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ይናገራሉ

ሉሲዎቹ በሴካፋ ሴቶች ዋንጫ በምድብ ሁለት ከሩዋንዳ እና ታንዛኒያ ጋር ተደልድለዋል፡፡ ጂንጃ ከተማ ላይ ለሚካሄደው ውድድርም ቅዳሜ ወደ ስፍራው ያቀናል፡፡

ሶከር ኢትዮጵያ ከጉዞው በፊት ከግብ ጠባቂዋ ሊያ ሽብሩ ፣ አምበሏ ብርቱካን ገብረክርስቶስ እና አጥቂዋ ሎዛ አበራ ጋር ቆይታ አድርጋለች፡፡

picsart_1473416844872

“ጥሩ ነገር ለማምጣት እንጥራለን” ሊያ ሽብሩ

ስለዝግጅት

“ዝግጅት በጣም ጥሩ ነበር፡፡ ወደ 20 ቀን ሆኖናል ዝግጅት ከጀመርን፡፡ ወደ አዲስ አበባ ከመጣን ሁለተኛ ቀናችን ነው፡፡ አየሩ ትንሽ ይከብዳል፡፡ ዴሬዳዋ ሙቀት ስለሆነ በዛው ወደ ዩጋንዳ ብንሄድ ጥሩ ነበር፡፡ ነገር ግን እዚ አንዳንድ ነገሮችን መጨረስ ስለሚያስፈልግ ወደ አዲስ አበባ መጥተናል፡፡ ሁሉም ነገር ጥሩ ነው፡፡”

ስለታሰበው ውጤት

“በብሄረዊ ቡድን ያለው ነገር ደስ ይላል፡፡ ያው ለውጤት ነው የምንሄደው፡፡ ምክንያቱም ይህ ውድድር ሲዘጋጅ ለመጀመሪያ ግዜ ነው፡፡ በዚህ ውድድር ላይ ተካፋይ በመሆኔ ደስ ብሎኛል፡፡ ስኬታማ ብንሆን ደግሞ ትልቅ ታሪክ የምናስመዘገብ ይሆናል፡፡ ለዚህም ዝግጁ ነን፡፡ ጥሩ ነገር ለማምጣት እንጥራለን፡፡”

ወደ ብሄራዊ ቡደን መመለስ

“እኔ ረጅም አመት እንደመጫወቴ አሁንም እቀጥላለው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ብቃት ነው ዋናው፡፡ ረጅም ግዜ መጫወት ያለመጫወት አይደለም፡፡ ይህ አቅም እስካለ ድረስ እንጫወታለን፡፡”

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ቡድን ውስጥ አለመካተቷ

“ይህ የአሰልጣኙ አመለካከት ሊሆን ይችላል፡፡ ያው ኮከብ ተብለህ አለመጠራት ትንሽ ይከብዳል፡፡ ያው ጥያቄው ለአሰልጣኙ ቢሆን ይሻላል፡፡”

picsart_1473416792374

“ጥሩ የሰራ ሜዳ ላይ አሸንፎ ይወጣል” ብርቱካን ገብረክርስቶስ

ስለዝግጅት

“ዝግጅታችን ያው ወደ 15 ቀን አድርገናል፡፡ በጣም ጥሩ ዝግጅት እያደረግን ነው፡፡”

ከአፍሪካ ዋንጫው ውጪ መሆን እና ስለሴካፋ

“አዎ ከአፍሪካ ዋንጫው መውጣታችን በጣም ቆጭቶናል፡፡ ሆኖም ግን ለ2016 ሴካፋ ዋንጫ የመጀመሪያ እንደመሆኑ መጠን ታሪክ ሰርተን ማለፍ እንፈልጋለን፡፡ እኛም ታሪክ ሰርተን ኢትዮጵያን ስሟን ማስጠራት እንፈልጋለን፡፡ በዛም ቁጭት ጠንክረን እየሰራን ነው፡፡ እንደቡድን ውጤት አምጥተን ሃገራችንን አስጠርተን የታሪክ ተጠቃሽ መሆን ነው የምንፈልገው፡፡”

ስለ ተጋጣሚዎቻችን

“ስለተጋጣሚዎቻችን ያገኘነው እምብዛም መረጃ የለም፡፡ ከዚህ በፊት ታንዛኒያ እናውቀው ነበር፡፡ ምናልባት ታንዛኒያን እንደምናውቀው ሆኖ ላይጠብቀን ይችላል፡፡ በጣም ጠንክሮ ነው ሊመጣ የሚችለው፡፡ ማንም ቆሞ እንደማይጠብቀን ሁሉ እኛም ጠንክረን እየሰራን ነው፡፡ ጥሩ የሰራ ሜዳ ላይ አሸንፎ ይወጣል፡፡”

picsart_1473416752414

” ዩጋንዳ ላይ የተሻለች ሎዛ ሆኜ መቅረብ እፈልጋለሁ”

ስለ ዝግጅት

” ዝግጅታችን በጣም  ጥሩ ነበር፡፡ በድሬደዋ በነበረን ጊዜ ጥሩ የሚባሉ ልምምዶችን ስንሰራ ቆይተናል፡፡ አሰልጣኞቻችን የሚሰጡንን ነገር በአግባቡ ለመተግበር ስንሰራ ነበር፡፡ በአጠቃላይ የነበረን ቆይታ ጥሩ ነበር፡፡ ”

የቡድኑ መንፈስ

” የቡድን ህብረታችን በጣም አስደሳች ነው፡፡ በሜዳም ሆኘ ከሜዳ ውጭ ያለን ህብረት መልካም ነው፡፡ ”

ዋንጫ ስለ ማንሳት

” በግሌ የተሳካ የውድድር አመት አሳልፌያው፡፡ በታሪክም የመጀመርያ የሆነውን ይህን ውድድር ላይ በግሌ በቻልኩት አቅም የምችለውን ሁሉ ማድረግ እፈልጋለው፡፡ ያንንም አደርገዋለው ብዬ ነው የማስበው፡፡ ፈጣሪም ይረዳኛል፡፡ ዩጋንዳ በሚካሄደው ውድድር ላይ የተሻለች ሎዛ ሆኜ በመቅረብ ለኔም ብቻ ሳይሆን ለሀገሬ ከፍተኛ አስተዋፆ አድርጌ መመለስ ነው የምፈልገው፡፡ እንደ ቡድን ሁላችንም የምናስበው እዛ ሄደን ቻምፒዮን መሆን ነው፡፡ ምክንያቱም ለቀጣይ ጊዜ ጥሩ የሆነ ታሪክ መስራት እንፈልጋለን ”


[socialpoll id=”2385802″]

[socialpoll id=”2385807″]

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *