ወደ ዩጋንዳ የሚያመሩት 20 ተጫዋቾች ተለይተዋል

ዩጋንዳ በምታስተናግደው የመጀመርያው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ የሚካፈለው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ነገ ወደ ስፍራው ያመራል፡፡

አሰልጣኝ መሰረት ማኒ ወደ ዩጋንዳ ይዘዋቸው የሚጓዟቸውን 20 ተጫዋቾች የለዩ ሲሆን 4 ተጫዋቾችን ከጉዞው አስቀርተዋል፡፡

የደደቢቶቹ ሰናይት ቦጋለ እና ኤደን ሽፈራው ፣ የሲዳማ ቡናዋ አረጋሽ ጸጋ እና የሀዋሳ ከተማዋ አዲስ ንጉሴ ከጉዞው የቀሩት ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ወደ ዩጋንዳ የሚያቀኑት 20 ተጫዋቾች

ግብ ጠባቂዎች

ሊያ ሽብሩ (ነፃ) ፣ ማርታ በቀለ (መከላከያ) ፣ ታሪኳ በርገና (ድሬዳዋ ከተማ)

ተከላካዮች

አትክልት አሸናፊ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ መስከረም ካንኮ (ደደቢት) ፣ ምህረት መለሰ (መከላከያ) ፣  ጥሩአንቺ መንገሻ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ፅዮን እስጢፋኖስ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ እፀገነት ብዙነህ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ አሳቤ ሙሶ (ዳሽን ቢራ)

አማካዮች

እመቤት አዲሱ (መከላከያ) ፣ ብርቱካን ገብረክርስቶስ (ደደቢት) ፣ ፍቅርተ ብርሃኑ (መከላከያ) ፣ ብሩክታዊት ግርማ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ህይወት ደንጊሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ሰርካለም ቦጋለ (ዳሽን ቢራ)

አጥቂዎች

ሎዛ አበራ (ደደቢት) ፣ ረሂማ ዘርጋ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ሽታዬ ሲሳይ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ መዲና አወል (ቅድስት ማርያም ዩ.)

በተያያዘ ዜና ሉሲዎቹ 26 የልኡካን ቡድን በመያዝ ነገ 04:00 ላይ ወደ ዩጋንዳ የሚበሩ ሲሆን ካምፓላ ከደረሱ በኋላ የ180 ኪሜ የመኪና መንገድ አድርገው ውድድሩ ወደሚደረግበት ጂንጆ ከተማ ይገባሉ፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ በሴካፋው ውድድር የሚጠቀምበት አዲስ መለያ ከይፋዊው የትጥቅ አቅራቢ ኤሪያ ተዘጋጅቶላቸው የሚጫወቱም ይሆናል፡፡

እሁድ በሚገመረው ውድድር ኢትዮጵያ ከብሄራዊ ቡድኗ ባሻገር በአንድ ዳኛ ብቻ የምትወከል ሲሆን ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ወይንሸት አበራ ብቸኛዋ የኢትዮጵያ ተወካይ ናት፡፡


[socialpoll id=”2385802″]

[socialpoll id=”2385807″]

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *