ሉሲዎቹ በዩጋንዳ የመጀመርያ ልምምዳቸውን አከናውነዋል

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ረፋድ ላይ በጂንጆ ከተማ የመጀመርያ ልምምዳቸውን አከናወነዋል፡፡

በታሪክ የመጀመርያ የሆነውን የሴቶች የሴካፋ ዋንጫ ተሳትፎ ለማድረግ 26 የልኩአን ቡድን በመያዝ ትላንት ወደ ዩጋንዳ ያቀኑት ሉሲዎቹ ኢንቴቤ ከደረሱ በኋላ የ120 ኪሜ አድካሚ የመኪና ላይ ጉዞ በማድረግ ጂንጆ ከተማ ቢደርሱም የጠበቃቸው የማረፊያ ክፍል አስገራሚ ነበር፡፡ ማረፊያው ደረጃውን ያልጠበቀና በአንድ ክፍል ውስጥ ከ10 በላይ መተኛዎች ያሉት ክፍል ነበር ።

picsart_1473608677556

በሁኔታው የተደናገጡት ሉሲዎቹ ከኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ግንኙነት በመፍጠር አፈጣኝ መልስ አግኝተው ማዳ የተሰኘ ሆቴል በጊዜያዊነት አርፈዋል፡፡

ሁሌም በሚያዘጋጃቸው ውድድሮች እንከን የማያጣው ሴካፋ ለመጀመርያ በሚካሄደው የሴካፋ ዋንጫ ተመሳሳይ ግድፈቶች እየተስተዋለበት ይገኛል፡፡

picsart_1473608736778

ሉሲዎቹ ዛሬ ረፋድ ላይ የመጀመርያ ልምምዳቸውን ያከናወኑ ሲሆን ቀለል ያሉ ልምምዶች የመርሐግብራቸው አካል ነበር፡፡

ብሄራዊ ቡድናችን የመጀመርያ የምድብ ጨዋታ አራፊ በመሆናቸው የመጀመርያ ጨዋታቸውን የፊታችን ረቡዕ ከሩዋንዳ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ጋር የሚያደርጉ ይሆናል፡፡



ለመረጃዎች እና ፎቶዎች የተባበረን ጋዜጠኛ ዳግም ዝናቡን እናመሰግናለን፡፡


[socialpoll id=”2385802″]

[socialpoll id=”2385807″]

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *