በሴካፋ የሴቶች ዋንጫ 2ኛ ቀን ታንዛኒያ ድል ቀንቷታል

ዩጋንዳ በማስተናገድ ላይ የምትገኘው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ሁለተኛ ቀኑን ሲይዝ በምድብ ለ ታንዛኒያ ሩዋንዳን 3-2 አሸንፋለች፡፡ በንጁሩ ቴክኒካል ማዕከል በተደገረው ጨዋታ ከምድብ አንድ ከተደረጉት ጨዋታዎች የተሻለ ፉክክር ታይቶበታል፡

አሻ ራሺድ ሁለት ግቦች ለኪሊማንጃሮ ኩዊንሶቹ በማስቆጠር ወሳኝ ሚናን ተወጥታለች፡፡ ራሺድ በአምስተኛው ደቂቃ የሩዋንዳ ተከላካዮች የሰሩትን ስህተት ተጠቅማ ታንዛኒያን መሪ ስታደርግ አብደላ ስቱማኢ መሪነቱን ወደ ሁለት ከፍ አድርጋለች፡፡ ሺ አማቩቺ በሚል ስም የሚታወቁት ሩዋንዳዎች የፈጠሩት ጫና ከዕረፍት በፊት ሁለት ግቦችን እንዲያስቆጥሩ ረድቷቸዋል፡፡ አን ማሪ ኢባጋሪ በቅጣት ምት እና የታንዛኒያዋ ፋቱማ ባሺሪ በራሷ ግብ ላይ ያስቆጠሩት ግብ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ 2 አቻ በሆነ ውጤት ወደ መልበሻ ክፍል እንዲያመሩ አስችሏል፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ የጨዋታ ብልጫ የነበራቸው ሩዋንዳዎች በተደጋጋሚ በመልሶ ማጥቃት በታንዛኒያዎች ሲፈተኑ የነበረ ሲሆን የራሺድ ግብም ሽንፈትን እንዲቀምሱ አድርጓል፡፡

ውጤቱ ታንዛኒያን ወደ ግማሽ ፍፃሜ የምታደርገውን ጉዞ ሲያሳምር ሩዋንዳ ኢትዮጵያን የምትገጥምበት ጨዋታ ወሳኝነቱ ጨምሯል፡፡ ሉሲዎቹ ሺ አማቩቢዎቹን ረቡዕ የሚገጥሙ ይሆናል፡፡

ፎቶ፡ ሱፐርስፖርት


[socialpoll id=”2385802″]

[socialpoll id=”2385807″]

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *