የዝውውር ዜና | 03-01-2009
ፋሲል ከተማ የዳሽኑ ተከላካይ ያሬድ ባየህን የግሉ ሲያደርግ የኮከቡ አብዱልራህማን ሙባረክን ኮንትራት አድሷል፡፡
አማራ ውሃ ስራን ለቆ ባለፈው ክረምት ዳሽንን የተቀላቀለው ያሬድ በአጭር ጊዜ በሊጉ ከሚገኙ ምርጥ ተከላካዮች አንዱ መሆን የቻለው ያሬድ ወደ ደደቢት ለማምራት ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም ሌላኛው የከተማው ቡድን ፋሲልን መቀላቀል ምርጫው አድርጓል፡፡
ፋሲል ከተማ በዚህ ክረምት ከዳሽን ቢራ ያስፈረማቸው ተጫዋቾች 3 ደርሰዋል፡፡ አጥቂው ኤርሚያስ ኃይሉ እና የመስመር ተከላካዩ አምሳሉ ጥላሁን አሁን ደግሞ ያሬድ ባየህ ዳሽንን ለቀው ፋሲልን ተቀላቅለዋል፡፡
ፋሲል ከተማ በዘንድሮ የውድድር አመት ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ የክለቡን ወሳኝ ተጨዋቾችን ውል በማደስ ላይ ይገኛል፡፡ ከነዚህም መካከል የአመቱ የከፍተኛ ሊግ ኮከብ ተጨዋች ሆኖ ያጠናቀቀው አብዱልራህማን ሙባረክ ውሉን ያደሰ ተጫዋች ሆኗል፡፡
ከክለቡ ጋር በተያያዘ የዝውውር ዜና አምስት የውጭ ዜጋ ተጨዋቾችን በማምጣት የሙከራ ጊዜ ሰጥቶ ለማየት ለክለቦችና ተጨዋቾች ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን በቅርብ ቀናት መጥተው የተሳካ የሙከራ ጊዜ የሚያሳልፉትን ለማስቀረት እንቅስቃሴ መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡
የከፍተኛ ሊጉ የምድብ እና አጠቃላይ አሸናፊ ለሆነው ፋሲል ከተማ የክልሉ መንግስት የገንዘብና ለተጨዋቾች ማመላለሻ ዘመናዊ አውቶቢስ በስጦታ ሲያበረክት በጎንደር ከተማ ከፍተኛ የሆነ አቀባበል ሊደረግለት እንደታሰበም ታውቋል፡፡
ፋሲል ከተማ የአዲሱ የውድድር ዘመን ዝግጅቱን ከመስከረም 6 ቀን 2009 አንስቶ በቢሸፍቱ ከተማ ይጀምራል፡፡
[socialpoll id=”2385802″]
[socialpoll id=”2385807″]