ወልድያ 9 ተጫዋቾች አስፈርሟል

 የዝውውር ዜና | 03-01-2009 

ወልድያ 9 አዳዲስ ተጫዋቾች ማስፈረሙን በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ይፋ አድርጓል፡፡

በከፍተኛ ሊጉ ፋሲል ከተማን ተከትሎ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ያደገው ወልድያ ዘግይቶ ወደ ዝውውር ገበያው ቢገባም በርካታ ተጫዋቾችን ማስፈረም ችሏል፡፡

ግብ ጠባቂው ዳዊት አሰፋ ከንግድ ባንክ ፣ ተከላካዮቹ ያሬድ ዘውድነህ ከዳሽን ፣ ዳንኤል ደምሴ ከባህርዳር ከተማ ፣ ፍሬው ብርሃን ከድሬዳዋ ከተማ ፣ ሐብታሙ ሽዋለም ከአማራ ውሃ ስራ ፤ አማካዩ ምንያህል ይመር ከዳሽን እንዲሁም አጥቂዎቹ ጫላ ድሪባ ከአዳማ ፣ አንዱአለም ንጉሴ ከ ሲዳማ እና ኤሪክ ኮልማን ከሙገር የፈረሙ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ወልድያ የአዲሱ የውድድር ዘመን ዝግጅቱን በዚህ ሳምንት የሚጀምር ሲሆን በአዲስ አበባ እና ወልድያ ዝግጅቱን እንደሚያከናውን ታውቋል፡፡


[socialpoll id=”2385802″]

[socialpoll id=”2385807″]


picsart_1473774112526

1 Comment

Leave a Reply