ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት | 04-01-2009
ተጠናቀቀ | ኢትዮጵያ 3-2 ሩዋንዳ
3′ 64′ ሎዛ አበራ 71′ መስከረም ካንኮ|45′ ሙኪሺማና ዶሮቲ 70′ ኒግቤዋራ ሲፋ ግሎሪያ
ተጠናቀቀ!!!!
ጨዋታው በኢትዮጵያ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ሉሲዎቹ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማለፋቸውን ከወዲሁ ሲያረጋግጡ ሁለቱንም ጨዋታ የተሸነፉት ሺ አማቩቢዎቹ ከውድድሩ ተሰናብተዋል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ሩዋንዳ
87′ ፍሎረንስ ኢማኒዛባዮ ወጥታ ካላይቴ ኢራዱካ ገብታለች፡፡
ቢጫ ካርድ
85′ ሎዛ አበራ ከኢትዮጵያ የመጀመርያውን የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክታለች፡፡
81′ ሩዋንዳዎች የሞከሩትን ኳስ የኢትዮጵያ ተከላካዮች ተረባርበው አውጥተውታል፡፡
ጎልልል!!! ኢትዮጵያ
71′ መስከረም ካንኮ በድጋሚ ኢትዮጵያን መሪ አድርጋለች፡፡ 3-2
ጎልል!!!! ሩዋንዳ
70′ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ አምበሏ ኒግቤዋ ግሎሪያ በግንባሯ በመግጨት ከመረብ አሳርፏለች፡፡ 2-2
ጎልልል !!!! ኢትዮጵያ
64′ ሎዛ አበራ ከሽታዬ ሲሳይ የተሻገረላትን ኳስ ተጠቅማ ኢትዮጵያን ወደ መሪነት መልሳለች፡፡
ቢጫ ካርድ
59′ የሩዋንዳ አምበል ኒባንግዌ ግሎሪያ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክታለች፡፡
53′ ከማዕዘን የተሻማውን ኳስ ረሂማ በግንባሯ በመግጨት ሞክራ ሄሌኔ አውጥታዋለች፡፡
49′ ብሩክታዊት ከርቀት የመታችው ኳስ ሄሌኔ ወደ ውጪ አውጥታዋለች፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
48′ መዲና አወል ወጥታ ረሂማ ዘርጋ ገብታለች
ተጀመረ!!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡
እረፍት!!
የመጀመርያው አጋማሽ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
ተጨማሪ ደቂቃ
የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
ጎልልል!! ሩዋንዳ
45′ ከማዕዘን የተሻማውን ኳስ ሙኪሺማና ዶሮቲ ገጭታ ከመረብ አሳርፋለች፡፡
43′ በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ውስጥ በመግባት ሎዛ አበራ የሞከረችው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
31′ ከመስከረም የተሻገረውን ኳሰ ሽታዬ ሲሳይ ሞክራ ግብ ጠባቂዋ ሄሌኔ አድናዋለች፡፡
30′ ብሩክታዊት ግርማ በረጅሙ ወደ ግበብ የሞከረችው ኳስ አግዳሚውን ታክከኮ ወጥቷል፡፡
29′ የኢትዮጵያ አጥቂዎች በተደጋጋሚ በጨዋታ ውጪ አቋቋም ላይ እየተገኙ ነው፡፡
24′ አኔ ማሪ በድጋሚ የመታችው ቅጣት ምት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
20′ አኔ ማሪ የመታችውን ቅጣት ምት ሊያ ሽብሩ አውጥታዋለች፡፡
10′ ሎዛ ከሳጥኑ ጠርዝ የመታችውን ኳስ ግብ ጠባቂዋ ሄሌኔ በቀላሉ ተቀጣጥራዋለች፡፡
ጎልልልል!!!!! ኢትዮጵያ
3′ ሎዛ አበራ ከሽታዬ ሲሳይ የተቀበለችውን ኳስ ከሳጥን ውጪ አክርራ በመምታት ግብ አስቆጥራለች፡፡
1′ በአንድ ደቂቃ ውስጥ ሁለቱም ቡድኖች በጨዋታ ውጪ እንቅስቄሴ ፊሽካ ተነፍቶባቸዋል፡፡
ተጀመረ!
ጨዋታው በሩዋንዳ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡
10:01 ቡድኖቹ ሰላምታ በመለዋወጥ ላይ ይገኛሉ፡፡
09:59 የአትዮጵያ ብሄራዊ መዝሙር እየተዘመረ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ አሰላለፍ
1 ሊያ ሽብሩ
3 መስከረም ካንኮ – 4 ጥሩአንቺ መንገሻ – 5 ፅዮን እስጢፋኖስ – 17 እፀገነት ብዙነህ
12 ብሩክታዊት ግርማ – 6 እመቤት አዲሱ – 11 ብርቱካን ገብረክርስቶስ (አምበል)
10 ሽታዬ ሲሳይ – 7 ሎዛ አበራ – 8 መዲና አወል
ተጠባባቂዎች
21 ማርታ በቀለ ፣ 15 ፍቅርተ ብርሃኑ ፣ 16 ሰርካዲስ ጉታ ፣ 2 አትክልት አሸናፊ ፣ 9 ረሂማ ዘርጋ ፣ 14 ህይወት ደንጊሶ ፣ 16አሳቤ ሙሶ
የሩዋንዳ አሰላለፍ
1 ኡዊዜይማና ሄሌን
13 ኡዋማህሮ ማርክሌር- 17 ኒባግዊሬ ግሎሪያ (አምበል) – 5 ሙካማና ክሌመንት – 3 ኡዋሪዌሴ ጁዳ
16 ካሊምባ አሊስ – 8 ኢማኒዛባዮ ፍሎረንስ – 10 ኒይራህፋስ ጄኔ – 11 ኢባንጋርዬ አኔ ማሪ
14 ሙኪሺማና ዶሮቲ – 12 ሙካታንጋሪና ጆሊና
10:20 የኢትዮጵያ ቡድን ጨዋታ ወደሚደረግበት ሜዳ እየገባ ይገኛል፡፡
(ፎቶ – አሸር ኮሙጌሳ)
ይህን ጨዋታ የምናቀርብላችሁ ከልሳን ሴቶች ስፖርት ቀጥታ የሬድዮ ስርጭት እና ከተለያዩ ድረገጾች በምናገኘው መረጃ ነው፡፡