የሴቶች እግርኳስ | 05-01-2009
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አዲሱ የውድድር ዘመን ጥቅምት 27 ቀን 2009 እንደሚጀመር ታውቋል፡፡
ፌዴሬሽኑ ለክለቦች በላከው ደብዳቤ መሰረት የውድድሩን እጣ የማውጣት ስነስርአት መስከረም 24 ቀን 2009 እንደሚያከናውን ሲያስታውቅ የክለቦች ምዝገባ እና ፍቃድ ከመስከረም 18-26 ይከናወናል፡፡
ተሳታፊ ክለቦች ለዳኞች እና ታዛቢዎች የሚከፈለውን ገንዘብ ከመስከረም 15 እስከ ጥቅምት 5 እንዲያጠናቅቁ ቀነ ገደብ የወጣላችሁ ሲሆን የተጫዋቾች ምዝገባ እስከ ውድድሩ መጀመር ድረስ ይቆያል፡፡
በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን 17 ክለቦች በሁለት ዞን ተከፍለው ውድድር ያካሄዱ ሲሆን በዘንድሮው አመት ቁጥሩ እስከ 22 ሊደርስ እንደሚችል ተገምቷል፡፡ አምና ከተሳተፉት መካከል ሲዳማ ቡና እና ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ ላይሳተፉ እንደሚችሉ ሲጠበቅ እንደ አአ ከተማ እና ጅማ አባቡና ያሉ አዳዲስ ቡድኖች ይካተታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡