ሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ፡ ኢትዮጵያ ከ ታንዛንያ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

 ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት | 06-01-2009 


ተጠናቀቀ | ኢትዮጵያ 0-0 ታንዛንያ


ታንዛንያ በእጣ የምድብ ለ ቀዳሚ ሆና አጠናቃለች፡፡ ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜው ኬንያን ትገጥማለች፡፡

እጣ
አምበሎቹ አሻ ረሺድ እና ሎዛ አበራ የምድቡን የበላይ የሚለይ እጣ እያወጡ ይገኛሉ፡፡

ተጠናቀቀ!!
ጨዋታው ካለ ግብ ተጠናቋል፡፡ የምድቡን የበላይ ለማወቅ እጣ ይወጣል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
ጨዋታው ሊጠናቀቅ የተጨመሩ 4 ደቂቃዎች ብቻ ይቀራሉ፡፡

90′ አብዱላ ስቱማይ ከማዕዘን ምት የተሻገረውን ኳስ ሞክራ ወደ ውጭ ወጥቷል፡፡

88′ ጨዋታው በአቻ ውጤት የሚጠናቀቅ ይመስላል፡፡ በዚህ ውጤት ከተጠናቀቀ የምድቡን የበላይ ለመለየት እጣ ይወጣል፡፡

ቢጫ ካርድ
84′
 ካሚስ ማይሙና በሽታዬ ላይ በሰራችው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክታለች፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
83′
ረሂማ ዘርጋ ወጥታ መዲና አወል ገብታለች፡፡

82′ ዶኒሲያ ዳንኤል የመታችው ቅጣት ምት የግቡን አግዳሚ ታኮ ወጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
76′
አምበሏ ብርቱካን ገብረክርስቶስ ወጥታ ፍቅርተ ብርሃኑ ገብታለች፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ታንዛንያ
69′
ሃፒ ሄንዝሮን ወጥታ አና ሄብሮን ገብታለች፡፡

63′ ሽታዬ ሲሳይ የሞከረችውን ኳስ ግብ ጠባቂዋ ፋቲማ አውጥታለች፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ታንዛንያ
61′
አምበሏ ሶፊያ ሙዋሲኪሊ ወጥታ አሚና አሊ ገብታለች፡፡

49′ ረሂማ ዘርጋ የሞከረችው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ ካለግብ ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡

34′ አንቶኒ አናስታዚያ ከርቀት የመታችውን ኳስ ሊያ ሽብሩ ጨርፋው የግቡን አግዳሚ ለትሞ ተመልሷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ታንዛንያ
27′
ፋዲላ ሃማድ ወጥታ ሸሪዳ ቦኒፌስ ገብታለች፡፡

25′ የኢትዮጵያ አጥቂዎች በታንዛንያ ተከላካዮች ላይ ጫና በመፍጠር ላይ ይገኛሉ፡፡

16′ ረሂማ ዘርጋ በግንባሯ ገጭታ የሞከረችውን ኳስ ግብ ጠባቂዋ ፋቲማ መልሳዋለች፡፡

13′ ታንዛንያ በተደጋጋሚ የማዕዘን ምት እያገኙ ነው፡፡ 4 ተከታታይ የማዕዘን ምቶችን ቢያገኙም ኢላማ መጠበቅ አልቻሉም፡፡

6′ ሎዛ አበራ ከሳጥኑ አቅራቢያ የመታችውን የቅጣት ምት ፋቲማ ወደ አውጥታዋለች፡፡

4′ ህይወት ደንጊሶ ከርቀት የመታችውን ኳስ ፋቲማ ኦማሪ ይዛዋለች፡፡

ተጀመረ!

ጨዋታው ተጀምሯል፡፡

09:55 የሁለቱም ብሄራዊ ቡድኖች የህዝብ መዝሙር በመዘመር ላይ ይገኛል፡፡


የኢትዮጵያ አሰላለፍ

1 ሊያ ሽብሩ

3 መስከረም ካንኮ – 4 ጥሩአንቺ መንገሻ – 5 ፅዮን እስጢፋኖስ – 17 እፀገነት ብዙነህ

12 ብሩክታዊት ግርማ – 14 ህይወት ደንጊሶ – 11 ብርቱካን ገብረክርስቶስ (አምበል)

10 ሽታዬ ሲሳይ – 7 ሎዛ አበራ – 9 ረሂማ ዘርጋ

ተጠባባቂዎች
21 ማርታ በቀለ ፣ 15 ፍቅርተ ብርሃኑ ፣ 16 ሰርካዲስ ጉታ ፣ 2 አትክልት አሸናፊ ፣ 8 መዲና አወል ፣ 6 እመቤት አዲሱ ፣ 16 አሳቤ ሙሶ

የታንዛኒያ አሰላለፍ

ፋቲማ ኦማሪ

ሶፊያ ምዋሲኪሊ (አምበል) አንቶኒ አናስታዚያ – ኢሳ ፋቱማ – ፋዲላ ሃማድ

ዳንኤል ዶኒሲያ – ሀፒ ሄንዝሮን – አሻ ራሺድ – አብዳላ ስቱማይ 

ሪቻርድ ዌማ – ካሚስ ማይሙናይህን ጨዋታ የምናቀርብላችሁ ከልሳን ሴቶች ስፖርት ቀጥታ የሬድዮ ስርጭት እና ከተለያዩ ድረገጾች በምናገኘው መረጃ ነው፡፡

3 Comments

  1. O! With Kenya? But don’t give up Lucy. You can. #Loza_Abera is best!

Leave a Reply