ቻምፒየንስ ሊግ፡ ዛማሌክ አንድ እግሩን ወደ ፍፃሜው አስገብቷል

 የአፍሪካ እግርኳስ | 06-01-2009 

የ2016 ኦሬንጅ የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የግብፁ ዛማሌክ የሞሮኮውን ዋይዳድ ካዛብላንካን 4-0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ወደ ፍፃሜ የሚያደርገውን ጉዞ አሳምሯል፡፡ በግብፅ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ አሌክሳንደሪያ በሚገኘው ቦርጅ ኤል አረብ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዘ ኋይት ናይትሶቹ ዋይዳድ ላይ ብልጫ መውሰድ ችለዋል፡፡

በመጀመሪያው አጋማሽ የ2-0 መሪነትን ይዘው ወደ መልበሻ ክፍል ያመሩት ዛማሌኮች በሁለተኛው አጋማሽ ተጨማሪ ሁለት ግቦች አክለው ዋይዳድ ካዛብላንካ ከወዲሁ የመልሱን ጨዋታ ተራራ የመውጣት ያህል እንዲከብደው አድርገዋል፡፡ ሺካባላ በአምስተኛው ደቂቃ በግምት ከ25 ሜትር ርቀት የመታው ኳስ ዛማሌክን መሪ ሲያደርግ አይመን ኸፍኒ በዋይዳድ ግብ ክልል ያገኘውን ኳስ ወደ ግብመት ቀይሮ መሪነቱን ወደ ሁለት አስፍቷል፡፡ ባሰም ሞሪስ ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ ሶስተኛው ሲያክል ሙስጠፋ ፋቲ በፍፁም ቅጣት ምት የማሳረጊያውን ግብ አስገኝቷል፡፡ በ2002 ራጃ ካዛባላንካን ካሸነፈ በኃላ የአፍሪካ ቻምፒዮን ሆና ለማያውቀው ዛማሌክ ውጤቱ መልካም የሚባል ነው፡፡ ዛማሌክ ከ11 ዓመት በኃላ ለመጀመሪያ ግዜ የፍፃሜ ግማሽ ጨዋታውን ያደረገ ሲሆን በ2005 በከተማ ተቀናቃኙ አል አሃሊ 4-1 በሆነ አጠቃላይ ውጤት ተሸንፎ ከውድድር መውጣቱ ይታወሳል፡፡

 

የአርብ ውጤት

ዛማሌክ (ግብፅ) 4-0 ዋይዳድ አትሌቲክ ክለብ (ሞሮኮ)

(5’ ሺካባላ 18’ አይመን ኸፍኒ 49’ ባሰም ሞርሲ 73’ ሙስጠፋ ፋቲ)

Leave a Reply